የSAVE THE CHILDREN INTERNATIONAL (አለም አቀፍ የህፃናት አድን ድርጅት) ያገለገሉ ተሸርካሪዎች እና ሞተር ሳይክሎች ግልፅ ጨረታ

Save-The-Children-Logo-2

Overview

  • Category : Motorcycles & Bicycles Sale/ Rent & Purchase
  • Posted Date : 10/15/2022
  • Phone Number : 0945555550
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 11/04/2022

Description

SAVE THE CHILDREN INTERNATIONAL (አለም  አቀፍ  የህፃናት  አድን  ድርጅት) ያገለገሉ ተሸርካሪዎች እና ሞተር  ሳይክሎች ግልፅ  ጨረታ

ቢ ዲ አር  ኤም  ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል/ማህበር  በአዲስ  አበባ፡  ኢትዮጵያ የሚገኘውን የአለም  አቀፍ  የህፃናት አድን  ድርጅት በመወከል  ባለቤትነታቸው የአለም  አቀፍ  የህፃናት  አድን  ድርጅት የሆኑ ያገለገሉ ተሸርካሪዎች እና  ሞተር  ሳይክሎች በግልፅ  ጨረታ  ለመሸጥ   ቅዳሜ  ጥቅምት   26  ቀን  2015  ዓ/ም  5፡00  ሠዓት  ግልፅ ጨረታ  ያካሂዳል።

ተሽከርካሪዎቹ  እና  ሞተር   ሳይክሎች  ለማየትና   ለመጫረት የሚፈልጉ  ተጫራቶች  ከሰኞ  ጥቅምት   7  ቀን 2015   ዓ/ም  እስከ  አርብ  ጥቅምት   25  ቀን  2015   ዓ/ም  ከጠዋቱ  3:00  እስከ  10:00  ሲኤምሲ ሚካኤል ቤተክርስትያንና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶስየሽን ህንፃ  አጠገብ  በሚገኘው  የድርጅቱ መጋዘን  በተቀመጠው የሰሌዳ  ጊዜ መመዝገብ መመልከትና የጨረታ  ማስከበሪያ  ሲ ፒ ኦ ማስያዝ  ይችላሉ።

ለመጫረት  ፍላጎት    ያለው    ማንኛውም    ግለሰብ   ይሁን   ድርጅት  ብር   500    በመክፈል  መመዝገብና ለሚጫረባትቸው ለእያንዳንዱ የመኪና  ጨረታ  መደብ  ለመኪና  ብር  250,000 (ሁለት  መቶ  ሀምሳ  ሺ  ብር) ለሞተር   ሳይክል   30,000   (ሰላሳ  ሺ  ብር)  ለጨረታ   ማስከበሪያ   በባንክ  በተረጋገጠ ቼክ  (ሲ  ፒ  ኦ)  በSAVE THE  CHILDREN  INTERNATIONAL   ስም   እስከ   አርብ   ጥቅምት   25   ቀን   2015   ዓ/ም   10:00   ሰዓት መመዝገብና የጨረታ  ማስከበሪያ  ሲፒኦ  ማስያዝ  ይኖርባቸዋል።

አሸናፊዎች  ለአሸነፉት ጨረታ   መደብ   ሙሉውን  ክፍያ   ጨረታው   ከተካሄደበት  ቀን  አንስቶ   ባሉ  ቀጣይ አምስት የስራ  ቀናት  ውስጥ  ማለት  እስከ  አርብ  ህዳር  2  ቀን  2015  ዓ/ም  10፡00  ሰአት  ሙሉን  ክፊያው በSAVE THE CHILDREN INTERNATIONAL Commercial Bank of Ethiopia, ሂሳብ  ቁጥር  1000031079342

ቀሪውን   ገንዘብ  መክፈል ይኖርባቸዋል። በተቀመጠው ጊዜ  ገደብ  መክፈል ያልቻሉ ተጫራቶች ያስያዙት የጨረታ  ማስከበሪያ  ገንዘብ  ያጣሉ።

ቢ  ዲ  አር  ኤም  ትሬድንግ  ኃ/የተ/የግል/ማህበር  ለተሸጡ  ተሽከርካሪዎች  ምንም   አይነት   ሃላፊነት   ወይም ዋስትና   አይወስድም። አሸናፊዎች  ለገዙት   ተሽከርካሪ  ወይም  ሞተር   ሳይክል   በኢትዮጵያ  መንግስት  ህግና ደንብ  መሠረት ለመንግስት መከፈል ያለባቸው  የግብር  የታክስ  የቀረጥ  ግዴታዎችና ተያያዥ የስም  ማዘዋወሪያ የቦሎ  ውዝፍና  ሌሎች  ወጪዎች በገዢ  የሚሸፈኑ ሲሆን  እነዚህ  ወጪዎች ከሽያጭ  ዋጋ  የማይቀነሱ  ይሆናል።

  • ሁሉም ተሸከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ  እና  ቦታ  እንዲሁም በማይመለስ   መልኩ   ይሸጣሉ። ድርጅቱ ከላይ የተቀመጡት መስፈርቶች ሳያሟሉ   ወይም  ለቀረበው   የጨረታ   መደብ  ተመጣጣኝ   ዋጋ  አልተሰጠም ብሎ ካመነ  ከተጫራቶች የተሰጠው  ዋጋ  ውድቅ  የማድረግ  መብቱ  የተጠበቀ  ነው።
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ  ካገኘ  ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ  የመሰረዝ  መብቱ  የተጠበቀ  ነው።

ለበለጠ  መረጃ  በ0945555550 ወይም  በ0907767777 ይደውሉ