ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ. ለሰጠው የብድር ማካካሻ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 መሠረት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 12/24/2022
- Phone Number : 0115581204
- Source : Reporter
- Closing Date : 01/13/2023
Description
ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ.
የቤት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ 002/2015
ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ. ለሰጠው የብድር ማካካሻ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 መሠረት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረቱ ባለቤት ስም | የንብረቱ ዓይነት/የሚሰጠው አገልግሎት | የቦታው ስፋት በካ.ሜትር | የካርታ ቁጥር | ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ | የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር | ||
ከተማ | ክ/ከተማ | ወረዳ | |||||||
1 | ኮንኮርዲያ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማ | አቶ የሱፍ በረዲን መሐመድ | ሕንጻ (ቅይጥ) | 250 | K04/1/47/338/389/3854/02 | አዲስ አበባ | ኮልፌ ቀራንዮ | 03 | 27,540,122.26 |
ስለሆነም፡-
- ንብረቶቹን ማየት የሚፈልግ ሁሉ በሚያመቻቸው ጊዜ በባንኩ በቅሎቤት ቅርንጫፍ በኩል ከላይ በሰንጠረዡ በተገለጸው አድራሻ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋት 3፡00 – 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 – 10፡00 ሰዓት ድረስ በመገኘት ንብረቶቹን ማየት ይቻላል፡፡ ስልክ ቁጥር 0114 674068 / 0114 70 4426 በቅሎቤት ቅርንጫፍ፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ በ15 /አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፣
- ተጫራቾች ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ በባንኩ ዋናው መ/ቤት ናሽናል ታውር ሕንጻ 11ኛ ፎቅ (ስታዲየም ከኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ) በሚገኘው እስከ ጥር 01 ቀን 2015 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዛወር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
- ለመንግስት የሚከፈል የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ማንኛውም ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ በንብረት ማስተላለፍ ሂደት የሚኖር ክፍያ እና ሌሎች ማንኛውንም ክፍያዎች ገዢው ይከፍላል፡፡
- የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና ኘሮሲጀር የሚያሟላ ተጫራች ባንኩ ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
- ለበለጠ ማብራሪያ ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት በስልክ ቁጥር 0115 58 12 04/0115 31 81 56 ደውሎ መረዳት ይቻላል፡፡
- ባንኩ ንብረቶቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡