ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ ያገለገሉ ቋሚ የቢሮ መገልገያ እቃዎች የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

Debub-Global-Bank-SC-logo-3

Overview

  • Category : Disposal Sale
  • Posted Date : 03/18/2021
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 04/05/2021

Description

ያገለገሉ ቋሚ የቢሮ መገልገያ እቃዎች የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 የጨረታ ቁጥር 034-2020/21

 

ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን፣ የካውንተር ንቃዮች፣ የፓርቲሽን ንቃዮች፣ ቁርጥራጭ አልሙኒየም ብረቶች እና የመሳሰሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን የጨረታ መመሪያ እና መመዘኛዎች የሚያሟላ ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች መወዳደር ይችላል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ. ስታዲየም ቅርንጫፍ በመክፈል እና የገቢ ደረሰኝ ይዘው በመቅረብ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ስታዲየም ከኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ ናሽናል ቢዝነስ ሴንተር 11ኛ ፎቅ ንብረትና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ በመቅረብ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡

የጨረታ ዋጋው ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ወይም ተርን ኦቨር ታክስ (TOT) ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 (አምስት ሺ ብር) በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

እቃዎቹን ጠመንጃ ያዥ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት በቶታል ማደያ እና በእምነት ሬስቶራንት መካከል ባለሙ ቅያስ ገባ ብሎ በሚገኘው የባንኩ ዋና ንብረት ክፍል በአካል በመገኘት ማየት ይቻላል፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 0114705368 ወይም 0118494208 መደወል ይችላሉ፡፡

ግልጽ ጨረታው መጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ጠዋት 4፡00ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ጠዋት 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባንኩ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡

ተጫራቾች እቃዎቹ ባሉበት ቦታ በአካል በመገኘት እና እቃዎቹን በደንብ ተመልክተው ዋጋ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡

ባንኩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- በደቡብ ግሎባል ባንክ ንብረትና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ስልክ ቁጥር 0115581204 ወይም 0115318156 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

Send me an email when this category has been updated