ዳሎል ኦይል አክስዮን ማህበር በኦሮሚያ ክልል በወለንጪቲ ከተማ ቀበሌ 01 የሚገኘውን የዳሎል ኦይል አ.ማ የነዳጅ ማደያ ለኦፕሬተር / የሽያጭ ወኪል አወዳድሮ መስጠት ይፈልጋል፡፡

Dalol-oil-s.c-logo-1

Overview

 • Category : Fuel & Related
 • Posted Date : 06/08/2021
 • Phone Number : 0116672501
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/28/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ዳሎል ኦይል አክስዮን ማህበር በኦሮሚያ ክልል በወለንጪቲ ከተማ ቀበሌ 01 የሚገኘውን የዳሎል ኦይል አ.ማ የነዳጅ ማደያ ለኦፕሬተር / የሽያጭ ወኪል አወዳድሮ መስጠት ይፈልጋል፡፡

 • ለመወዳደር የሚፈልጉ አመልካቾች
 1. በዘርፉ ልምድ ያካበቱ ቢሆኑ ይመረጣል፡፡
 2. የነዳጅ ማደያው ስራ የሚጠይቀው የመስሪያ ካፒታል (ገንዘብ) በግላቸው የማቅረብ አቅም ያላቸው
 3. የነዳጅ ማደያውን የእለት ተእለት ስራ በቂ ጊዜ ሰጥተው በግላቸው ማንቀሳቀስ የሚችሉ

ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ግለሰቦች የማመልከቻ ሰነዱን ዳሎል ኦይል አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ቦሌ መድሀኒያለም ፊት ለፊት የሚገኘው ሕብረት ኢንሹራንስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ መውሰድ እና ሰነዱን ሞልተው መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡

ይህ ጨረታ ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 20 የስራ ቀናት በ 21/10/2013 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቦሌ መድሐንያለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ሕብረት ኢንሹራንስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮአችን ይከፈታል፡፡

 • ከላይ ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ በኋላ የሚቀርብ የማመልከቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 • ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ውድድሩን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • ከማመልቻ ሰነድዎ ጋር የሚከተሉት ደጋፊ መረጃዎች አባሪ መደረግ አለባቸው፡፡
 • የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ (ፓስፖርት) ፎቶ ኮፒ
 • ያለዎትን የገንዘብ አቅም የሚያሳይ ወቅታዊ የሆነ ቢያንስ የ6 ወር ተቀማጭ /ተንቀሳቃሽ የባንክ ሂሳብዎን የሚያሳይ የባንክ ስቴትመንት
 • በዘርፉ ያለዎትን ልምድ የሚያሳይ ማስረጃ 

ለበለጠ መረጃ

ዳሎል ኦይል አ.ማ

የስልክ ቁጥሮች፡ 0116 67 25 01 /02 /03 /04

አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ

Send me an email when this category has been updated