ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ. ለምርት እና ለሽያጭ ስራ ለመጠቀም ከተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚያስመጣቸውን መለዋወጫዎችን፣ የምርት ግብዓቶችን ፣ ፍሪጆችን ፣ የላብራቶሪ ግብአቶች፣ ማሽኖችን፣ የድራፍት መቅጃ ማሽኖችን እና አክሰሰሪዎችን ወዘተ በዘርፉ ልምድ ካላቸው አስመጭዎች ጋር በተመጣጣኝ ዋጋ ውል ወስዶ መስራት ይፈልጋል፡፡

Dashen-Brewery-logo

Overview

  • Category : Purchases
  • Posted Date : 09/10/2021
  • Phone Number : 0116591249
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 09/30/2021

Description

Ref. No: DBSC/PD/            /21

የአቅራቢዎች ምዝገባ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ. ለምርት እና ለሽያጭ ስራ ለመጠቀም ከተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚያስመጣቸውን መለዋወጫዎችን፣ የምርት ግብዓቶችን ፣ ፍሪጆችን ፣ የላብራቶሪ ግብአቶች፣ ማሽኖችን፣ የድራፍት መቅጃ ማሽኖችን እና አክሰሰሪዎችን ወዘተ በዘርፉ ልምድ ካላቸው አስመጭዎች ጋር በተመጣጣኝ ዋጋ ውል ወስዶ መስራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከፋብሪካችን ጋር መስራት የምትፈልጉ ድርጅቶች የኩባንያችሁን ፕሮፋይል በማቅረብ በድርጅታችን የአቅራቢዎች ዝርዝር ሠነድ ላይ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ከፕሮፋይላችሁ ጋር የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

1) ታደሰ የንግድ ፍቃድ

2) የተጨማሪ እሴት ታክስ መለያ ሠርትፊኬት

3) የታክስ ክሊራንስ

4) በዘርፉ ያላችሁን የስራ ልምድ የሚያሳይ ማስረጃ

5) የካፒታል መጠን የሚያሳይ ማስረጃ (Annual turnover & financial position) at least three years)

6) ድርጅታችውን የሠው ኃይል እና አደረጃጀት የሚያሳይ ማስረጃ

አቅራቢዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 20 (ሃያ) ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን ሠነድ አሟልተው አዲስ አበባ በሚገኘው የዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት (22 የቱሪስት ንግድ ስራ ድርጅት አጠገብ) ከሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ፕሮፋይላችሁን ማቅረብ የምትችሉ ሲሆን ማስታወቂያው ከመስከረም 2/2014 እስከ መስከረም 20/2014 ዓ.ም ድረስ አየር ላይ የሚቆይ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116591249 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል