ድርጅታችን ትራኮን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጀሞ 1 ሆፕ ዩኒቨርስቲ ጀርባ በሚገኘው ትራኮን ሪል ስቴት ያስገነባውን ቤቶች ለመሸጥ ማስታወቂያ አሰርቶ በቴሌቪዝን ማስታወቂያውን ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

Tracon-Trading-Logo-2

Overview

 • Category : Entertainment & Docu
 • Posted Date : 06/03/2021
 • Phone Number : 0989098625
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/15/2021

Description

ትራኮን ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግል ማህበር

በትራኮን ሪል ስቴት ማስታወቂያ ለማሰራት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር፡20/2021/1

ድርጅታችን ትራኮን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጀሞ 1 ሆፕ ዩኒቨርስቲ ጀርባ በሚገኘው ትራኮን ሪል ስቴት ያስገነባውን ቤቶች ለመሸጥ ማስታወቂያ አሰርቶ በቴሌቪዝን ማስታወቂያውን ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ማስታወቂያ በመስራት ልምድ ያላቸውን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

መስራት የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

 1. ተጫራቾች የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፍቃድና የቫት ተመዝጋቢ ሆነው በዚህ ዓመት የታደሰ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የመጫረቻ ዋጋችሁን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ትራኮን ሪል ስቴት ከግንቦት 30/2013 ዓ.ም እስከ ሰኔ 8/2013 ዓ.ም ድረስ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
 2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 100 ብር/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከትራኮን ታወር መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
 3. የጨረታ ዋስትና ብር ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2 ፕርሰንት በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
 4. የጨረታ አሸናፊው በአንድ ሳምንት ውስጥ ውሉን ጨርሶ ስራወን መጀመር አለበት፡፡
 5. ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለጨረታ ማስገቢያ የተዘጋጀውን ቅፅ፤ ከግንቦት 30/2013 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 – 6፡00 እና ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 – 11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 – 6፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
 6. ተጫራቾች የሰሩትን ማስታወቂያ በፍላሽ ወይም በሲዲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 7. ጨረታው ሰኔ 8/2013 ዓ.ም ከጠዋት 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ትራኮን ሪል ስቴት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በኮቪድ 19 ኮሮና በሽታ ምክኒያት መገኘት አይጠበቅባቸውም፡፡
 8. ተጫራቾች በሪል ስቴት ቤት ሽያጭ ማስታወቂያ ወይም በሌላ ስራ የሰሩት ካለ በፍላሽ ወይም በሲዲ አምጥተው ማሳየት ይችላሉ፡፡

– ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም

ለበለጠ መረጃ

ጥቁር አንበሳ ጀርባ ትራኮን ታወር ዜሮ ወለል  –

ስ.ቁ 0989098625/0923930134/0930034955