ድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሙሉጌታ ዘለቀ ህንጻ አጠገብ የሚገኘውን የግል ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ህንጻ ላይ ለባንክ፣ ለንግድና ለቢሮ አገልግሎት አመቺ የሆኑ ያልተያዙ ክፍሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

Commercial-Nominees-logo-2

Overview

  • Category : House & Building Rent
  • Posted Date : 10/09/2022
  • Phone Number : 0111569992
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 10/24/2022

Description

   ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ

 Commercial Nomminees PLC

የጨረታ ማስታወቂያ

CN/NCB/05/2015

ድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከግል ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ጋር በተደረገው የህንጻ አስተዳደር ውል መሰረት በመገናኛ፣ ወረዳ 7፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት፣ ሙሉጌታ ዘለቀ ህንጻ አጠገብ የሚገኘውን የግል ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ህንጻ ላይ ለባንክ፣ ለንግድና ለቢሮ አገልግሎት አመቺ የሆኑ ያልተያዙ ክፍሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 50.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-11፡00) ማግኘት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የሚከራየውን ቢሮ ሁኔታ ከላይ በተገለጸው አድራሻ የሚከራየው ህንጻ በሚገኝበት ቦታ በአካል በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡

ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከታች በተጠቀሰው አድራሻና የኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዋና መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ

ቦሌ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር 011-1-569992

አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ