ጀሞ ሁለገብ ሸማቾች ኃላ/የተ/የህብረት ሥራ ማኀበር ከአየር ጤና በዓለም ባንክ በአምቦ መውጫ መንገድ ዳር ሙሉ ግቢ ባለበት ሁኔታ የተሻለ ዋጋ ለሚያቀርብ ተከራይ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : House & Building Rent
 • Posted Date : 12/08/2021
 • Phone Number : 0113486136
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/29/2021

Description

የቤቶች እና የቦታ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

ጀሞ ሁለገብ ሸማቾች ኃላ/የተ/የህብረት ሥራ ማኀበር ከአየር ጤና በዓለም ባንክ በአምቦ መውጫ መንገድ ዳር ከወረዳ 4 ወጣቶች መዝናኛ ማዕከል ከፍ ብሎ ያለውን እና የቀድሞ ቁጥር 4 ትምህርት ቤት፣

 • አጠቃላይ ይዞታው      ከ1600 ካሬ ሜትር በላይ
 • በብሎኬት የተገነቡ                          6 ክፍል ቤቶች
 • በላሜራ የተሰሩ      5 ክፍል ቤቶች
 • ደረቅ መፀዳጃ ቤቶች                 6 ክፍሎች
 • ባዶ ቦታ                           ከ1300 ካሬ ሜትር በላይ

የሆነውን ሙሉ ግቢ ባለበት ሁኔታ የተሻለ ዋጋ ለሚያቀርብ ተከራይ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው

 1. የቤቶቹንና የግቢውን ይዞታዎች የሚገልፀውን ፕላን እንዲሁም የተጫራቾች መመሪያና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜን (ከ2፡30 – 6፡30 ሰዓትን) ጨምሮ በማኅበሩ ዋና ጽ/ቤት ቀርበው የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡
 2. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ይኼንኑ ሰነድ በማሳየት ግቢውን መጎብኘት ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች ቢያንስ ለ2013 በጀት ዓመት የታደሰ ንግድ ፈቃድ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 4. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በሲፒኦ (cpo) ማቅረብ አለባቸው፡፡
 5. የጨረታ ሰነዳቸውን እስከ ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ብቻ በማኅበሩ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 6. ጨረታው በተዘጋበት ዕለት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀድሞው ቁጥር 4 ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ይከፈታል፡፡
 7. ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ጀሞ ሁለገብ ሸማቾች ኃላ/የተ/የህ/ሥራ ማኅበር

አድራሻ

ዓለም ባንክ አካባቢ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ትሮፒካል ቅርንጫፍ ያለበት ህንፃ 3ኛ ፎቅ

ስ.ቁ. 0113 48 61 36

Send me an email when this category has been updated