ጊፍት ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ያገለገሎ 4 (አራት) ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

gift-trading-logo-rreportertenders

Overview

 • Category : Disposal Sale
 • Posted Date : 03/28/2021
 • Phone Number : 0114655580
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 04/12/2021

Description

ድርጅታችን ጊፍት ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ያገለገሎ 4 (አራት) ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 1. ተሸከርካሪዎቹን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ቦሌ ከጌቱ ኮሜርሽያል ፊትለፊት በሐር ህንጻ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 907 መውሰድ ይችላሉ፡፡
 2. ይህማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 14 (አስራ አራት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሃያ ሁለት ከመክሊት ህንጻ ጎን ቅጥር ግቢ በአካል በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
 3. ተጫራቾችየተሸከርካሪዎቹን ይዞታ በማየት የሚሰጡትን ዋጋ በቁጥርና በፊደል መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም በፊደልና በቁጥር የተጻፈው ዋጋ ልዩነት የሚኖረው ከሆነ መ/ቤቱ ትልቁን ዋጋ በመያዝ ጨረታውን ያወዳድራል፡፡
 4. ተጫራቾችየጨረታ ሠነዱን ሞልተው የሚገዙበትን ዋጋ ቫትን (15%) ጨምሮ በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላትና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከመጋቢት 20 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ባሉ 14 (አስራ አራት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቦሌ ከጌቱ ኮሜርሽያል ፊትለፊት በሐር ህንጻ   9ተኛ ፎቅ በመሄድ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 5. ጨረታውሚያዚያ 4 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ቦሌ ከጌቱ ኮሜርሽያል ፊትለፊት በሐር ህንጻ   9ተኛ ፎቅ  ይከፈታል፡፡
 6. ሌሎችተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው፡፡
 7. ተጫራቾችየሚጫረቱበትን ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ሙሉ በሙሉ የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ከሚገዙበት ዋጋ ጋር ይታሰባል፡፡
 8. የጨረታ አሸናፊው ከጨረታው በኃላ ያሉትን የስም ማዘዋወሪያ ወጪዎች ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል፡፡
 9. አሸናፊዎችየጨረታው ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ንብረታቸውን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባያው ገቢ ይደረጋል፡፡
 10. ማንኛውምየመንግስት ዕዳ ቢኖር ሻጭ ይከፍላል፡፡
 11. ኩባንያውየተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ  ቦሌ ከጌቱ ኮሜርሽያ ፊት ለፊት በሐር ህንጻ   9ተኛ ፎቅ  

ቢሮ ቁጥር 907

ስልክ 011-4-65-55-80

 

 

Send me an email when this category has been updated