ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ለዋና መ/ቤት እና ለአብይ ቅርንጫፍ የኔትርወርክ ዝርጋታ ሥራ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

Global-Insurance-Company-S.C-logo-reportertenders

Overview

 • Category : Network Installation & Troubleshooting Service
 • Posted Date : 07/30/2022
 • Phone Number : 0912173404
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/12/2022

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)  ለዋና መ/ቤት እና ለአብይ ቅርንጫፍ የኔትርወርክ ዝርጋታ ሥራ ድርጅቶችን አወዳድሮ  ማሠራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ አገልግሎቱን የሚሰጡ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

 1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ፣ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ሱማሌ ተራ በሚገኘው ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ህንፃ 4ኛ ፎቅ የማይመለስ ብር 50/ሃምሣ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት ብቻ በሰም የታሸገ የመጫረቻ ሰነዶቻችሁን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በ20 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በሥራ ቀን ካልዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በካሽ ማስያዝ አለባቸው፡፡
 5. ተጫራቾች የሳይት ጉብኝት የማድረግ ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ኩባንያችን ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912 173404 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- ሱማሌ ተራ ተክለሃይማኖት ሆስፒታል ፊት ለፊት ግሎባል ኢንሹራንስ ህንፃ

ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)