ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) በዋና መስሪያ ቤቱ የ I.C.T Datacenter Power ሥራን ለማሰራት ከዚህ ጋር ተዛማጅ የሆነ ሥራ የሚሰሩ ሕጋዊ ኩባንያዎችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Global-Insurance-Company-S.C-logo-reportertenders

Overview

 • Category : Network Installation & Troubleshooting Service
 • Posted Date : 11/02/2022
 • Phone Number : 0111565850
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/21/2022

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) በዋና መስሪያ ቤቱ የ I.C.T Datacenter Power ሥራን ለማሰራት ከዚህ ጋር ተዛማጅ የሆነ ሥራ የሚሰሩ  ሕጋዊ ኩባንያዎችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

የጨረታ ዝርዝር መስፈርት

 1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
 2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ሱማሌ ተራ በሚገኘው ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ህንፃ 4ኛ ፎቅ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት ብቻ ዋናውን የቴክኒካል እና የፋይናሺያል ሰነዶችን በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች ለየብቻቸው አሽገው እንደገና ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድ ፖስታ በማሸግ እንዲሁም በተመሳሳይ መልኩ የቴክኒካልና የፋይናንሺያል ኮፒ ሰነዶችን በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች ለየብቻቸው አሽገው እንደገና ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድ ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ጨረታው በ20ኛው ቀን ኅዳር 12 ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ሕንፃ 4ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺ) ብር በባንክ በተረጋገጠ C. P. O (ሲ.ፒ. ኦ) ወይም በካሽ ማስያዝ  ይኖርባቸዋል፡፡
 6.   ተጫራቾች የሳይት ጉብኝት የማድረግ ግዴታ ይኖርባቸዋል::
 7. ኩባንያችን ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡-   ሱማሌ ተራ ተክለሃይማኖት ሆስፒታል ፊት ለፊት ግሎባል  ኢንሹራንስ ሕንፃ

ለበለጠ መረጃ   በስልክ ቁጥር 0111 565850 ግዥና ንብረት አስተዳደር ይደውሉ

ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)