ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 25ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ

Announcement
Global-Insurance-Company-S.C-logo-reportertenders

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 10/15/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/05/2022

Description

 ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

የባለአክሲዮኖች 25ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ

የግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ ባለአክሲዮኖች በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀፅ 393 (1) 394 እንደዚሁም በኩባንያው መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 8(3) መሠረት በሚደረገው 25ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንዲገኙ ጥሪ ተደርጓል፡፡ የግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ የተፈረሙና የተከፈለ ካፒታል እ.ኤ.አ ሰኔ 30 2022 ላይ ብር 175,734 ሚሊዮን፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለኩባንያው የተሰጠ ምዝገባ ቁጥር 23377/89፤ የኩባንያው ዋና መ/ቤት የሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጎበና አባጥጉ መንገድ ሱማሌ ተራ በሠራው የራሱ ሕንፃ ላይ ነው፡፡

ጠቅላላ ጉባኤዎቹ የሚካሄደው ቅዳሜ ጥቅምት ­­­26, 2015 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ ­­­ቦሌ መድሃኒያለም አደባባይ አጠገብ በሚገኘው ቤስት ዌስት ሆቴል ይካሄዳል፡፡

የስብሰባው አጀንዳ

 1. አጀንዳ ማጽደቅ፣
 2. ድምፅ ቆጣሪዎችን መሰየም፣
 3. ምልዓተ ጉባኤ መሟላትቱን ማረጋገጥ፣
 4. እ.ኤ.አ የ2021/22 በጀት ዓመት የተደረጉ የኩባንያውን የአክሲዮን ዝውውሮችን ማፅደቅና አክሲዮን የገዙ፣አዳዲስ ባለአክሲዮችን መቀበል፣
 5. እ.ኤ.አ የ2021//22 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፤
 6. እ.ኤ.አ 2021/22 የውጭ ኦዲተሮችን ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ
 7. ከላይ በተራ ቁጥር 5 እና 6 ላይ በቀረቡት ሁለቱ ሪፖርቶች ተወያይቶ ሪፖርቶቹን ማፅደቅ
 8. እ.ኤ.አ 2021/22 የኩባንያው የትርፍ ድልድል በተመለከተ በዳይሬክተሮች ቦርድ የቀረበውን ውሳኔ ሃሳብ መርምሮ መወሰን፣
 9. እ.ኤ.አ ከ2021/22 አንስቶ ለሶስት ተከታታይ አመታት የሚያገለግሎትን የውጭ ኦዲተሮችን መሾም እና የ2022/23 አበል ክፍያን መወሰን፤
 10. እ.ኤ.አ 2021/22 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ዓመታዊ የሥራ ዋጋ ክፍያና እና እ.ኤ.አ 2022/23 ወርሃዊ አበል ክፍያን መወሰን፣
 11. የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ አባላትን መምረጥ
 12. የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ፡

ማሳሰቢያ፡-

 1. በስብሰባው ላይ ለመገኘት ማይችሉ ባለአክሲዮኖች ሕጋዊ ውክልና በመስጠት ወይም በኩባንያው አማካኝነት የተዘጋጀውን የውክልና ቅፅ ከስብሰባው ቀን አስቀድሞ በመሙላት ተወካይ መሻምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በማቅረብ የስብሰባው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠትም ሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
 2. ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ወደ ስብሰባው ሲመጡ ኢትጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ ፓስፖርት ወይም የቀበሌ መታወቂያ ዋናውንና ኮፒ ይዘው መገኘት አለባቸው፡፡ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሆኑ ውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያረጋግጥ የቢጫ ካርድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

በዳሬክቶሬት ቦርድ ትዕዛዝ