ግራንድ ማይክሮፋይናስ ተቋም አ.ማ ፍላጎት ያላቸውን የውጪ ኦዲት ድርጅቶች ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ለ 3 (ሶስት) ተከታተይ የበጀት ዓመት የአክሲዮን ማህበሩን ሂሳብ ኦዲት እንዲያደርጉ ይጋብዛል፡፡

Grand-microfinance-Institution-share-company-logo

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 09/10/2021
 • Phone Number : 0114705102
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 09/26/2021

Description

ግራንድ ማይክሮፋይናስ ተቋም አክሲዮን ማህበር

የውጪ ኦዲተር ሥራ ጨረታ

ግራንድ ማይክሮፋይናስ ተቋም አ.ማ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ቀልጣፋ የብድርና ቁጠባ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ተቋም ሲሆን፤ ፍላጎት ያላቸውን የውጪ ኦዲት ድርጅቶች ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ለ 3 (ሶስት) ተከታተይ የበጀት ዓመት የአክሲዮን ማህበሩን ሂሳብ ኦዲት እንዲያደርጉ ይጋብዛል፡፡ በመሆኑም በጨረታው የሚሳተፉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

 1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ክሊራንስ፤ የቫት ምዝገባና የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፤
 2. በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ፈቃድ የተሰጠውና፤ የታደሰ የምዝገባ ፈቃድ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፤
 3. የሂሳብ ኦዲት ስራ ለመስራት የሚያስችል ህጋዊ ፈቃድ ያለዉ፤
 4. በሥራዉ ላይ በተለይም የአነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ኦዲት በማድረግ በቂ ልምድ ያለው፤
 5. የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት የተከተለ ሂሳብ ኦዲት ያደረገና ልምድ ለማቅረብ የሚችል፤
 6. ተጫራቾች የዉጪ ኦዲት አገልግሎት የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የክፍያዉ 10% C.P.O በግራንድ ማይክሮፋይናስ ተቋም አ.ማ ስም አሰርተው ማቅረብ የሚችሉ፤
 7. ግራንድ ማይክሮ ፋይናስ አ.ማ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ መስከረም 16 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ድረስ በዋና መስርያ ቤታችን በደብረዘይት መንገድ በቅሎቤት ኖክ ማደያ አጠገብ በሚገኘዉ ጋራድ ሞል 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 2 በሥራ ሰዓት በአካል በመቅረብና የሚሰሩበትን ዝርዝር ማብራርያና ዋጋ (Technical and Financial Proposal) ከአስፈላጊ ሰነዶች ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ግራንድ ማይክሮፋይናስ ተቋም አክሲዮን ማህበር

ስልክ 0114705102