ግራንድ ማይክሮ ማይናንስ ተቋም አ.ማ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ተሸከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Grand-microfinance-Institution-share-company-logo

Overview

  • Category : Vehicle Sale
  • Posted Date : 11/21/2022
  • Phone Number : 0114705102
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 12/02/2022

Description

ግራንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ

  የተሸከርካሪ ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

ግራንድ  ማይክሮ ማይናንስ  ተቋም አ.ማ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ተሸከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. Suzuki Dzire 2022 ሞዴል መኪና ብዛት አንድ
  2. 200 cc ፣ 175 cc እና 150 cc ሞተር ሳይክል ብዛት ሁለት

በዚሁ መሰረት ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1 ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ መታወቂያ፣ የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2 ተጫራቾች የተሽከርካሪውን አጠቃላይ ዝርዝር የሚገልፅ፣ ዋጋ እና የሚያስረክቡበትን ቀን ጠቅሰው የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ጧት ከ2፡00 – 6፡00 እና ከሰዓት ከ7፡00 – 11፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በመምጣት ማስገባት ይችላሉ፡፡

3 ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸው፣ ፊርማቸውንና የድርጅቶቻቸውን ማህተም ማሳረፍ አለባቸው፡፡

4   ድርጅቱ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡

አድራሻ፡-    

ደብረዘይት መንገድ በቅሎ ቤት አካባቢ ኖክ ማደያ ጋራድ ህንፃ 7ኛ ፎቅ

ስልክ፡-  +251 114705102