ጎህ ቤቶች ባንክ ለዋናዉ መ/ቤት እና አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች ለሚከፍታቸው አዳዲስ ቅርንጫፎች የጥብቃ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Security & Protection Equipment Guarding
- Posted Date : 02/27/2022
- Phone Number : 0116686833
- Source : Reporter
- Closing Date : 03/17/2022
Description
የጥበቃ አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ጎህ/አግጨ/001/14
- ጎህ ቤቶች ባንክ ለዋናዉ መ/ቤት እና አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች ለሚከፍታቸው አዳዲስ ቅርንጫፎች የጥብቃ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለአንድ (1) ዓመት በሚቆይ ኮንትራት ስምምነት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፤ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ፤ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ወቅቱን የጠበቀ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በዋናው መ/ቤት ቦሌ መንገድ ጃፓን ኢንባሲ በሚገኘው አብድሩፍ ህንፃ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር 5ኛ ፎቅ ላይ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመልስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ማግኘት ይቻላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታው በኋላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00(ሰላሳ ሺ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ደብዳቤ (ጋራንቲ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሽገ ኢንቨሎፕ በማድረግ እስከ መጋቢት 08 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት መጋቢት 08 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ጎህ ቤቶች ባንክ ዋናዉ መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ 6ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-668-68-33 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡