ጎመጁ ኦይል ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የድርጅቱ ንብረት የሆኑትን እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የነዳጅ ማደያዎችና ህንፃዎች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

Gomeju-Oil-reportertenders

Overview

 • Category : House & Building Rent
 • Posted Date : 12/26/2022
 • Phone Number : 0116501010
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/13/2023

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ጎመጁ ኦይል ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የድርጅቱ ንብረት የሆኑትን እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የነዳጅ ማደያዎችና ህንፃዎች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

 1. በባህር ዳር ከተማ ውስጥ በተለምዶ ዘንዘልማ አካባቢ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የሚገኘውን ጎመጁ ባህር ዳር ቁጥር 1 ነዳጅ ማደያና ህንፃዎቹ፤
 2. በባህር ዳር ከተማ ውስጥ በተለምዶ ጎርደማ አካባቢ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የሚገኘውን ጎመጁ ባህር ዳር ቁጥር 2 ነዳጅ ማደያና ህንፃዎቹ፤
 3. በሞጆ ከተማ ውስጥ በተለምዶ ደረቅ ወደብ አካባቢ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የሚገኘውን ጎመጁ ሞጆ ነዳጅ ማደያና ህንፃዎቹ፤

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ኩባንያዎች ወይም ግለሰቦች የነዳጅ ማደያዎቹንና ህንፃዎቹን አሁን ባሉበት ሁኔታ ለመከራየት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል።

 1. ተጫራቹ ነዳጅ ከምንጩ ወደ ማደያዎቹ በራስ ትራንስፖርት የማጓጓዝ አቅም ያለው መሆኑን በተረጋገጠ ማስረጃ ማሳየት የሚችል መሆን አለበት፡፡
 2. ተጫራቹ አገልግሎቱን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማስኬድ በቂ የገንዘብ አቅም ያለው መሆኑን ማሳየት የሚችል መሆን አለበት።
 3. ተጫራቹ የታደሰ የግል ወይም ድርጅታዊ ማንነትን፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የመኖርያ አድራሻ ወዘተ እና አስፈላጊ የሆኑ ዋናውንና ቅጂ ሰነዶችን ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
 4. ተጫራቹ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ/CPO ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
 5. ተጫራቹ የሚያቀርባቸውን የፋይናንስ እና የቴክኒካል ጨረታ ሰነዶች ለየብቻቸው በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
 6. ተጫራቹ የጨረታ ሰነዶቹን ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት አንስቶ እስከ ጥር 3 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላል፡፡
 7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 3 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
 8. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው የድርጅቱ አድራሻ በአካል በመቅረብ የመጫረቻ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፤

 • ጎመጁ ኦይል ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማ
 • ከቦሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት ጀርባ በእምነት ሬስቶራንት አጠገብ

ለተጨማሪ ማብራሪያ   + 251-116-50-10-10   +251-930-22-22-20/22