ጥረት በ2021 እ.ኤ.አ በጀት አመት በተለያዩ የስልጠና ርዕሶች በየደረጃው ላሉ አመራሮችና ሰራተኞች የስልጠና አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Tiret-logo

Overview

 • Category : Education & Training Services
 • Posted Date : 08/06/2021
 • Phone Number : 0582203701
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/23/2021

Description

 የጨረታ ቁጥር 02/ግል/21

 ቀን 05/08/2021 እ.ኤ.አ

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ጥረት በ2021 እ.ኤ.አ በጀት አመት በተለያዩ የስልጠና ርዕሶች በየደረጃው ላሉ አመራሮችና ሰራተኞች የስልጠና አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

 1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
 2. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ከዋናው ጋር የተገናዘበ የምስክር ወረቀት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ የሚችሉ፣
 3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ባህር ዳር አልማ ህንፃ ግራውንድ ጥረት ቢሮ ቁጥር G-05 በመቅረብ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
 4. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ከፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 3፡00 ተዘግቶ በ3:30 ስዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አልማ ህንፃ ግራውንድ ቢሮ ቁጥር G-10 ይከፈታል፤ ነገር ግን ባለመገኘታቸው ጨረታውን በስዓቱ ለመክፈት የሚከለክል የለም፡፡ ሆኖም የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋበት ቀን ክብረ በዓል እና ከስራ ቀን ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ስዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የስልጠና አገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 1 % በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፣
 6. ጥረት ማዕከል የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
 7. የሚገዙ የስልጠና አገልግሎቶችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፣
 8. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጥረት ማእከል ባህር ዳር አልማ ህንፃ ግራውንድ ጥረት ቢሮ ቁጥር G-05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582203701/0582263164/ በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፣
 9. በዚሁ ጨረታ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

የጥረት ኮርፖሬት ማዕከል ባህርዳር                        

Send me an email when this category has been updated