ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ የካሣ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎችና የተለወጡ የተሽከርካሪ አካላትን እንዲሁም ሌሎች ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Vehicle Sale
- Posted Date : 02/13/2023
- Closing Date : 02/26/2023
- Phone Number : 0111119771
- Source : Reporter
Description
ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ
የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን የካሣ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎችና የተለወጡ የተሽከርካሪ አካላትን እንዲሁም ሌሎች ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ተሽከርካሪዎችንና የተሽከርካሪ አካላትን እንዲሁም ሌሎች ንብረቶችን መግዛት የሚፈልጉ ሁሉ ቃሊቲ ቶታል ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት በካፍደም ሲኒማ ወደ ዉስጥ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካን አለፍ ብሎ በሚገኘው የኩባንያዉ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች ማቆያ ቦታ በቆሙበት ከየካቲት 06 ቀን 2015 ጀምሮ በመገኘትና በማየት የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊትለፊት በሚገኘው ዋና መ/ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ መጫረት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የካቲት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከጧቱ 4:00 ሰዓት በኩባንያው ዋና መ/ቤት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃ የመነሻ ዋጋዉን 10% (አስር በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም የጨረታ ማሰከበሪያው ለተሽከርካሪዎች ከብር 5,000.00 (አምስት ሺህ) እንዲሁም የተሽከርካሪ አካላት ላይ ከብር 500.00(አምስት መቶ) ማነስ የለበትም፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው፡፡
- በተሽከርካሪዎችና ሌሎች አካላት ላይ ከጨረታው በፊት ዕዳዎች ቢኖሩ በኩባንያው ይሸፈናል፡፡ በጨረታው ለተካተቱ ንብረቶች ከጨረታው በኋላ ያሉትን ማናቸውም ወጪዎች ገዥው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላሉ፡፡
- አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን መረከብ ዕቃዎቹንም ሙሉ በሙሉ ማንሳት አለባቸዉ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 111 97 71/70 ወይም 011 126 39 94 በመደወል ወይም ከላይ በተጠቀሰዉ ዋና መ/ቤት በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ