ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ በዋናው መ/ቤት ለሚያሰራው የመጋዘን ቁጥር 2 ግንባታ ስራ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሕንፃ ስራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Construction Service & Maintenance
- Posted Date : 06/05/2021
- Closing Date : 07/06/2021
- Phone Number : 0114340110
- Source : Reporter
Description
የመጋዘን ግንባታ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 013/2013
ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ በዋናው መ/ቤት ለሚያሰራው የመጋዘን ቁጥር 2 ግንባታ ስራ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሕንፃ ስራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ የስራ ተቋራጮች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- የግንባታ ስራ ፍቃድ ደረጃቸው 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በመስኩ የታደሰ እና ሕጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ በሚመለከተው መ/ቤት የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቃሊቲ መናኸሪያ አካባቢ ፣ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት፣ ከካፍደም ሲኒማ በኩል 700 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ከፋብሪካው የግዥ ዋና ክፍል የማይመለስ ብር 200 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡት ጨረታ ሰነድ ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል በሚል ተለይቶ ለየብቻው አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በፋብሪካው ግዢ ዋና ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ፋብሪካው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ
ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ
ዋና መ/ቤት ስልክ 011-4-34-01-10/011-4-34-40-06