ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ በዋናው መ/ቤት አርክቴክትና መሐንዲስ አማካሪ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Architects Service
- Posted Date : 06/05/2021
- Phone Number : 0114340110
- Source : Reporter
- Closing Date : 06/22/2021
Description
የግንባታ አማካሪነት የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 012/2013
ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ በዋናው መ/ቤት ለሚያሰራቸው ሁለት መጋዘኖች መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ግንባታዎች የኮንትራት አስተዳደር እና የግንባታ ቁጥጥር የሚሰራ ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ አርክቴክትና መሐንዲስ አማካሪ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ የስራ ተቋራጮች በጨረታ እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- የአርክቴክትና መሐንዲስ አማካሪነት የስራ ፍቃድ ደረጃቸው 4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በመስኩ የታደሰ እና ሕጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ በስራ መስኩ በሚመለከተው መ/ቤት የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቃሊቲ መናኸሪያ አካባቢ ፣ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት፣ ከካፍደም ሲኒማ በኩል 700 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ከፋብሪካው የግዥ ዋና ክፍል የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ፋይናንሺል እና ቴክኒካል በሚል ተለይቶ ለየብቻው አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በፋብሪካው ግዢ ዋና ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሰኔ 15 ቀን 2013 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት በእለቱ ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ፋብሪካው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ
ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ
ዋና መ/ቤት ስልክ 011-4-34-01-10/011-4-34-4006