ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ

Announcement
Tsehay-Industry-logo

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/07/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/03/2022

Description

የጉባኤ ጥሪ

በኢፌዲሪ የንግድ ህግ አንቀጽ 366,367,370,371 እና 372 መሠረት የፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ቅዳሜ ህዳር 24 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሆቴል ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች በሙሉ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ የአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

 • የማህበሩ ዋና ገንዘብ ፡ ብር 879,080,000.00
 • የማህበሩ የንግድ የምዝገባ ቁጥር ፡ AKK/AA/3/0007051/2011
 • የማህበሩ ዋና መ/ቤት የሚገኝበት አድራሻ፡ አዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 12

የጉባዔው አጀንዳዎች

 1. የጉባዔውን ረቂቅ አጀንዳዎች ማጽደቅ፣
 2. የአክሲዮን ዝውውሮች ስለማሳወቅ እና አዳዲስ አባላት ስለመቀበል፣
 3. የ2014 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማድመጥ፣
 4. የ2014 የሂሳብ ዘመን የውጭ ኦዲተር ሪፖርት ማድመጥ፣
 5. በዳይሬክተሮች ቦርድ እና በውጭ ኦዲተር ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 6. በ2014 የሂሳብ ዘመን የተጣራ ትርፍ ድልድል እና አከፋፈል ላይ ተወያይቶ ስለመወሰን፣
 7. የ2015 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን አባል ስለመወሰን፣
 8. የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ፣

ማሳሰቢያ፡-

በጉባኤው ዕለት ባለአክሲዮኖች ማንነታችሁን የሚገልፅ የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ወይም መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ይዛችሁ መቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡ ሥልጣን በተሰጠው አካል በስብሰባው ላይ ለመገኘትና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ስልጣን የተሰጣችሁ ተወካዮችም የውክልናውን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ይዛችሁ በመቅረብ በጉባዔው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

የፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ