ፈያ ኢንትግሬትድ ዲቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ከዚህ በታች የተገለጹትን አላቂ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 04/27/2021
 • Phone Number : 0115578114
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 05/08/2021

Description

ፈያ ኢንትግሬትድ ዲቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን

ድርጅታችን ፈያ ኢንተርግሬትድ ደቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን( መንግስታዊ ያልሆነ አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ላለፉት 20 ዓመታት በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ከመንግስትና አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን እየሰራ ያለ ህጋዊ የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ-አድራጎት ድርጅት ነው፡፡ አሁን ከUNOCHA/World Vision Ethiopia/EHF ባገኘነው Multi-Sectorial Response in Medresa IDP site of Buno Bedelle Zone of Oromia Region-Dedesa Woreda  Project ድርጅታችን ከዚህ በታች የተገለጹትን አላቂ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ/ቁ

የእቃው አይነት

ብዛት

1

 ጀሪካን 20 ሊትር ፒ ኤች ኢዲ ግሬድ ሲ ፕላስቲክ ታይፕ 45 ሚሊ ሜትር ስፋት የሚከፈት(Jerry-can 20 liter PHED food grade type of plastic, 45mm wide opening)

2376

 

2

የልብስ መዘፍዘፊያ 60 ሴ.ሜትር ዳያሜትር ስቴንልስ ስቲል (Washing basin 60cm diameter stainless steel)

1188

 

3

የልብስ ሳሙና 250 ግራም ጠንካራ በቀላሉ የማይርስ መሸፈኛ ያለውና የአገልግሎት ዘመን የተፃፈበት (Laundary soap 250gm,hard water resistant & package with labeled expiry date

5940

4

የገላ ሳሙና 100ግራም ጠንካራ በቀላሉ የማይርስ መሸፈኛ ያለውና የአገልግሎት ዘመን የተፃፈበት(Body soap 100gm,hard water resistant & package with labeled expiry date)

5940

 

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያማሉ ተጫራቾች በከፊል ወይም በሙሉ መጫረት ይችላሉ፡፡

 1. በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 2. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሁሉም አጠቃላይ ዋጋ 2 % (ፐርሰንት) በድርጅታችን (ፈያ ኢንተግሬትድ ዲቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን) ስም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ማቅረብ አለባቸው ከሚቀርበው አጠቃላይ ዋጋ 2%  (ፐርሰንት)  በታች ያስያዘ ከጨረታው ዉድድር ውጪ የሚደረግ ይሆናል፡፡
 3. ስለጨረታ የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 50 (ሀምሳ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጅምሮ ለተከታታይ አስር (10) ቀናት ከፈያ ኢንትግሬትድ ዲቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ዋናው መስሪያ ቤት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እንዲሁም የሚወዳደሩበትን እቃ ናሙና እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2013 ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ በመምጣት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
 5. ጨረታው ሚያዝያ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 6. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115578114 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
 7. ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 8. አሸናፊው ተጫራች ባሸነፈበት ዋጋ ያሸነፈበትን የእቃ ዝርዝር በማግስቱ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
 9. ለተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስረከቢያ ያስያዙት ገንዘብና ናሙና ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡  

ፈያ ኢንተርግሬትድ ደቨሎፕመንት ኦርጋንይዜሽን

አድራሻ: ሜክሲኮ ቀይ መስቀል አ.አ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት ከባልቻ ሆስፒታል ጀርባ ናዛሪን ቤተክርስቲያን 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር  24; ስልክ ቁጥር :+251 – 11 557-81-14