ፈጣን ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ አንድ ምድብ ሀ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር የአንድ ዓመት ሂሣብ የውጭ ኦዲተሮችን አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 05/27/2021
 • Phone Number : 0113698532
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/10/2021

Description

ሂሣብ ለማስመርመር

የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ

ፈጣን ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ አንድ ምድብ ሀ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር ከሐምሌ 1 ቀን 2012 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ ያለውን የአንድ ዓመት ሂሣብ የውጭ ኦዲተሮችን አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባችሁ፡፡

 1. ተጫራቾች በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የተፈቀደና የታደሰ የሙያ ብቃት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
 2. 2013 ዓ.ም. የታደሰ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፣
 3. ተጫራቾች ከዚህ በፊት ሂሣብ ለመመርመራቸው ከታወቁ ድርጅቶች ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ጀሞ መካኒሳ ሚካኤል በስተጀርባ ከሚገኘው መ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 9 ድረስ በመቅረብ የሂሣብ ሰነዶቹን በማየት የሚሠሩበትን ዋጋ ያቀርባሉ፡፡
 5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከመወዳደሪያ ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 7. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ ይከፈታል፡፡ /የመዝጊያው ሆነ የመክፈቻው ዕለት የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡/
 8. የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ማህበራትን ሂሣብ የዘጋ ቢሆን የተሻለ ይሆናል፡፡
 9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻችን፡

 • ጀሞ መካኒሳ ሚካኤል በስተጀርባ
 • የስልክ ቁጥር 0113- 69 85 32, 69 85 35,

Send me an email when this category has been updated