ፍቅር ለህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች መግዛት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 09/01/2021
 • E-mail : loveforchildrenfdco@gmail.com
 • Phone Number : 0113213192
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 09/10/2021

Description

ፍቅር ለህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት  መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ድርጅት ሲሆን ከቻይልድ ፈንድ ኢትዮጵያ ጋር በአጋርነት የሚሰራ ድርጅት ነዉ፡፡ ድርጅታችን በድርጅቱ ታቅፈዉ ለሚደገፉ ህጻናት፤ ወጣቶች እና የትምህርት ቤት ማህበረሰቦች ራሳቸዉን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል  የሚከተሉትን የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች መግዛት ይፈልጋል፡፡

 • የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር ብዛት 2,500 ሊትር (ቢያንስ 99% ማጽዳት የሚችል መሆን አለበት)
 • የሚታጠብ የፊት መሸፈኛ ጭንብል (Face Mask) ብዛት በቁጥር 2,500 ሁለት አርማ ያለበት (የድርጅቱ እና ) የአጋር ድርጅት)

በመሆኑም ተጫራቾች፡

 1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
 3. የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የሚገልጽ ማስረጃ ከገቢዎች ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ
 4. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር (10) የስራ ቀናት ሰነዳቸዉንና ማስረጃቸዉን የድርጅቱን ማህተም በማስቀመጥና በፖስታ በማሸግ እንዲሁም የፊት መሸፈኛዉን ናሙና በማያያዝ በድርጅቱ ጽ/ቤት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 5. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በአስረኛዉ ቀን ከጠዋቱ በ 4፡30 ላይ በግልጽ ይከፈታል
 6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2% በተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ገነንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል
 7. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታዉ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ
 8. ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
 9. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ
 10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚያስገቡት የድርጅቱ ጽ/ቤት በሚገኝበት አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ከመካኒሳ ወደ ቆሬ በሚወስደዉ መንገድ ወረዳ ሁለት ወጣት ማዕከል ፊት ለፊት በሚገኘዉ የቸሻየር ፋዉንዴሽን ግቢ ዉስጥ በሚገኘዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ይሆናል፡፡
 11. ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡
 12. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው አግባብ በራሳቸው ወጪ የድርጅታችን ቢሮ ድረስ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 011 321 31 92 / 011 321 10 27 ወይም በሞባይል ቁጥር 0911 12 13 37 መደወል ይችላሉ

በኢሜል፡ loveforchildrenfdco@gmail.com ይጠይቁ፡፡

ፍቅር ለህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት