ፍቅር ለህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት ለ 2015 ዓ.ም. በጀት ዓመት በዓየር ጤና ትምህርት ቤት የሚሰራ ጊቢን የማስዋብ ስራ / የግሪን ኤሪያ / የግንባታ ባለሙያዎችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

love-for-children-logo

Overview

 • Category : Construction Service & Maintenance
 • Posted Date : 08/15/2022
 • E-mail : loveforchildrenfdco@gmail.com
 • Phone Number : 00113213192
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/26/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ፍቅር ለህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት  መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ድርጅት ሲሆን ከቻይልድ ፈንድ ኢትዮጵያ ጋር በአጋርነት የሚሰራ ድርጅት ነዉ፡፡ ድርጅታችን ለ 2015 ዓ.ም. በጀት ዓመት በዓየር ጤና ትምህርት ቤት የሚሰራ  ጊቢን የማስዋብ ስራ / የግሪን ኤሪያ / የግንባታ ባለሙያዎችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል ፡-

በዚህም መሰረት ተጫራቾች፡

 1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የሚገልጽ ማስረጃ ከገቢዎች ጽ_ቤት ማቅረብ የሚችሉ
 3. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ማግስት ጀምሮ ለተከታታይ አስር (10) የስራ ቀናት ዉስጥ ሰነዳቸዉንና ማስረጃቸዉን የድርጅቱን ማህተም በማስቀመጥና በፖስታ በማሸግ በድርጅቱ ጽ_ቤት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 4. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት አስረኛዉ ቀን ከጠዋቱ በ 4፡30 ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2% በተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል
 6. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታዉ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ
 7. የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ጽ/ቤት በብር 100.00 በመግዛት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ፡፡
 8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ
 9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚያስገቡት የድርጅቱ ጽ_ቤት በሚገኝበት አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ከመካኒሳ ወደ ቆሬ በሚወስደዉ መንገድ ወረዳ ሁለት ወጣት ማዕከል ፊት ለፊት በሚገኘዉ የቸሻየር ፋዉንዴሽን ግቢ ዉስጥ በሚገኘዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 011 321 31 92 _ 011 321 10 27 ወይም በሞባይል ቁጥር 0911 12 13 37 መደወል ይችላሉ

በኢሜል፡ loveforchildrenfdco@gmail.com ይጠይቁ፡፡

ፍቅር ለህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት