ዘመን ባንክ አ.ማ ዝርዝራቸው ከዚህ በታች የተገለጹትን የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 10/09/2021
 • Phone Number : 0115575825
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/07/2021

Description

  የጨረታ ቁጥር፡ ZB/PD/02/2021

        የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታዎቂያ

ዘመን ባንክ አ.ማ ዝርዝራቸው ከዚህ በታች የተገለጹትን የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች ከታች በቀረቡት ማብራሪያዎች መሠረት በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

ተ.ቁ. የዕቃው ዓይነት ብዛት የዕቃዎቹ ሁኔታ
1 ያገለገለ ጀነሬተር (Cummins 220KVA) year of make 2008 1 ጥገና የሚፈልግ
2 የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ፈርኒቸሮች (ወንበር፣ ጠረጴዛ እና የመሳሰሉት) 21 አገልግሎት የሰጡ
3 የተለያዩ ያገለገሉ ዲስክቶፕ ኮምፒውተሮች ከነ ሞኒተሩ 33 አገልግሎት የሰጡ
4 የተለያዩ ፕሪንተሮች (8)፣ ፋክስ (2)፣ ስካነር (1)፣ ኮፒ ማሽን (1) እና ስካን ሽልድ (5) 17 አገልግሎት የሰጡ
5 ኤሌክትሪካል ካልኩሌተር (7)፣ የውሃ ማጣሪያ (3)፣ የእጅ መፈተሻ መሳሪያ (3)፣ 13 አገልግሎት የሰጡ
6 ቫኪውም ማጽጃ (Vacuum cleaner) 3 አገልግሎት የሰጡ
7 የተለያዩ የአየር ማቀዝቀዣ (Air Conditioner) 6 አገልግሎት የሰጡ
8 40” ቴሌቪዥን 1 አገልግሎት የሰጠ
9 የተለያዩ ያገለገሉ ጋዜጦች ከ500 ኪ.ግ በላይ አገልግሎት የሰጡ
10 ያገለገሉ አልሚኒየሞች፣ብረታብረቶች፣ጣውላዎች እና መሰል በጥቅል አገልግሎት የሰጡ
11 የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎች 70 አገልግሎት የሰጡ
12 ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች 30  
13 የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ፕሪንተር ቶነሮች 631 አገልግሎት የሰጡ
14 የተለያዩ የሴንተራል ዮ.ፒ.ኤስ ባትሪዎች  56 አገልግሎት የሰጡ
15 የተቃጠለ የሞተር ዘይት 2 በርሚል አገልግሎት የሰጡ

ማሳሰቢያ፡

 1. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃ በግልጽ በማመልከት የንብረቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይም በሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 2. ተጫራጮች ንብረቶቹን ቦሌ ዓለም ሲኒማ ጀርባ በሚገኘው የዘመን ባንክ ግቢ ውስጥ፤ ጀነሬተሩን ደግሞ ጎፋ “ስኩል ኦፍ ቱሞሮ” አካባቢ የሚገኘው የባንኩ መጋዘን ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ መመልከት ይቻላል፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ጥቅምት 01 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2014ዓ.ም ድረስ ቦሌ ዓለም ሲኒማ ጀርባ ከሚገኘው የውብዳር ህንጻ 4ኛ ፎቅ ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው በመግዛት መመልከት ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ በማድረግ የተጫረቱበትን ዕቃ ስም እና ተራ ቁጥር በመጻፍ እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ በባንኩ ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
 5. ጨረታው ጥቅምት 17 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተዘግቶ ወዲያውኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 6. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 7. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-557 58 25 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡