ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ ከዚህ በታች የተመለከቱትን የመገልገያ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Machinery Purchase
- Posted Date : 10/09/2021
- Phone Number : 0114340110
- Source : Reporter
- Closing Date : 11/06/2021
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 0012/2014
ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ ከዚህ በታች የተመለከቱትን የመገልገያ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ እነዚህም፡-
MIG Welding Machine, Grinder Machine, MIG Welding Torch with & without Coolant, MIG Welding Accessories, Cutting Disc, Grinding Disc & Leather Hand Glove እና ሌሎችም፡፡
በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለ ጨረታው የተዘጋጅውን ዝርዝር መግለጫ ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ.ም 5:00 ድረስ ከፋብሪካው የግዢ ዋና ክፍል ቢሮ የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች በመስኩ የታደሰ እና ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ እንዲሁም ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፣
- የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ለፋብሪካው ግዥ ዋና ክፍል ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ፋብሪካው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ
ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ
ዋና መ/ቤት ስልክ 0114-34-01-10- 011-434-40-06