ኤስ.ኦ.ኤስ. ሳህል ኢትዮጵያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና ሞተርሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Motorcycles & Bicycles Sale/ Rent & Purchase
- Posted Date : 10/09/2021
- Phone Number : 0114160391
- Source : Reporter
- Closing Date : 10/29/2021
Description
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ጨረታ ማስታወቂያ
ኤስ.ኦ.ኤስ. ሳህል ኢትዮጵያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና ሞተርሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በወጣ ከ3ኛው ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ጠብመንጃ ያዥ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘዉ የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) “ኤስ.ኦ.ኤስ. ሳህል ኢትዮጵያ” በሚል ስም አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ /Column/ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቬሎፕ /ፖስታ/ ለኤስ.ኦ.ኤስ. ሳህል ኢትዮጵያ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በሪፖርተር አማሪኛ እትም ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በሶስት/3/ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በአምስት/5/ ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለኤጀንሲው ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከኤስ.ኦ.ኤስ. ሳህል ኢትዮጵያ ዋና መ/ቤት የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ብር200.00 /ሁለት መቶ ብቻ/ እየከፈሉ ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናቶች ድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን በአስራ አምስተኛው ቀን ሰነዱ የሚሸጠው እስከ ጠዋቱ 4፡00ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
- ጨረታዉ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤስ.ኦ.ኤስ. ሳህል ኢትዮጵያ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች ሰነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ኤስ.ኦ.ኤስ ሳህል ኢትዮጵያ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማንኛውም ወጪ በገዢው የሚሸፈን ይሆናል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0114160391 ፣ 0114160400 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡