የእናት ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት በሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : House & Building Foreclosure
 • Posted Date : 10/09/2021
 • Phone Number : 0115586568
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/09/2021

Description

 ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

የእናት ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት በሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የተበዳሪ ስም የንበረት አስያዥ ስም አበዳሪ ቅርንጫፍ ለጨረታ የቀረበው ንብረት የንብረቱ ዝርዝር ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ሐራጁ የሚከናወንበት ጊዜ
 

አዛለች ተስፋዬ

 

 

አቶ ደረጄ አሻግሬ

 

 

ስንዱ ገብሩ መርካቶ ቅርንጫፍ

 

 

መኖሪያ ቤት

 

የቦታ ስፋት ካርታ ቁጥር ከተማ ወረዳ ቀበሌ  

2,050,000.00

 

ቀን ሰዓት
300m2

 

L.H.C.No:658/3394/97

 

ሰንዳፋ

 

በኬ

 

በኬ

 

 

ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ.ም

 

ከጠዋቱ 4፡00 -6፡00

የሐራጅ ደንቦች

 1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (¼ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
 2. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራቾች ምዝገባ አይካሄድም፡፡
 3. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበት ቀሪ ገንዘብ የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መክፈል አለበት፡፡ ባይከፍል ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
 4. ሐራጁ የሚካሄደው ንብረቱ በሚገኝበት በኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰንዳፋ በኬ ከተማ ነው፡፡
 5. በሐራጅ ላይ መገኝት የሚችሉት ተጫራቾች ተበዳሪ እና ንብረት አስያዦች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው፡፡
 6. ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን የስም ማዛወሪያ ጨምሮ ገዢው/አሸናፊው ይከፍላል፡፡
 7. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለሐራጅ የቀረበው ንብረት የሚገኘው በሰንዳፋ በኬ ከተማ ሲሆን ከለገጣፎ ወደ ሰንዳፋ በሚወስደው መንገድ ወዝ (WAS) ነዳጅ ማደያ አካባቢ ባለው ተቃራኒ አስፋልት መንገድ 150ሜ ገባ ብሎ ባለው ፒስታ መንገድ ላይ የሚገኝ ሲሆን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
 1. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-58-65-68 ወይም 0115-52-34-72 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡