መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የቃሊቲ ሥቶር የውስጥ ለውስጥ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት (21-01B) ለሰራተኞች ሰርቪስ እና ለፕሮጀክቱ አገልግሎት የሚውል 04 ሰው የመጫን አቅም ያለው ቪትዝ መኪና ፍቃድ ካላቸው ተጫራች ድርጅቶች ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Vehicle Rent
  • Posted Date : 10/13/2021
  • Phone Number : 0118350773
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 10/31/2021

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCE/17-03/02B/36/08/2021

ድርጅታችን መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የቃሊቲ ሥቶር የውስጥ ለውስጥ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት (21-01B) ለሰራተኞች ሰርቪስ እና ለፕሮጀክቱ አገልግሎት የሚውል 04 ሰው የመጫን አቅም ያለው ቪትዝ መኪና ፍቃድ ካላቸው ተጫራች ድርጅቶች ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከፕሮጀክታን ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በዚህም መሰረት ተጫራቾች፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡትን እንዲሁም ሌሎች ሕጋዊ ሰነዶችን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤
  2. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት በተጫራቾች መመሪያ አንቀጽ 9.2.2 መሰረት መሆን አለበት፤
  3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ዘውትር በሥራ ሰዓት እስከ ጥቅምት 20/2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  4. ጨረታው በዕለቱ ጥቅምት 20/2014 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ ቢሮ ይከፈታል፡፡ በዚህም መሰረት ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ ከሚገኘው ሃዮንዳይ ሞተርስ ወረድ ብሎ በልዩ ስሙ ጨሬ ሰፈራ የባጃጅ ተራ በሚገኘው ፕሮጀክታችን  ቢሮ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
  5. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡-   በስልክ ቁጥር፡- +251118350773

  ከሰላምታ ጋር