ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሎደር ጎማ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Tyre & Battery
  • Posted Date : 10/14/2021
  • Phone Number : 0116189602
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 10/22/2021

Description

የሎደር ጎማ ሽያጭ ጨረታ

ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከዚህ በታች የተመለከተውን የሎደር ጎማ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የጎማው ዓይነት መጠን(Size) ብዛት ይዞታው
1 ሎደር ጎማ( Top Trust) 20.5 x 25 PR 24 68 አዲስ

 

ጎማውን ለመመልከት የሚፈልጉ ተጫራቾች በስራ ሰዓት ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 9፡00 ሰዓት ታጠቅ በሚገኘው የማህበሩ መጋዘን በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ(CPO) የጠቅላላ ዋጋውን 2% ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ቦሌ መሰናዶ ት/ቤት ጀርባ በእምነት ሬስቶራንት አጠገብ በሚገኘው የማህበሩ ዋና መ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለጸላቸው በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ሙሉ ክፍያ በመክፈል ጎማውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያውን ፈጽመው ጎማውን መረከብ ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ጨረታው ይሰረዛል፡፡

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በሰባተኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ማህበሩ ስለ ጎማው አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0116-189602/0118-222265 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር