የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለወንጪ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት በግብዓትነት የሚውል የባለ 32 ጌጅ ኮርጌትድ ቆርቆሮ ዕቃው ግምዣ ቤት (stock) ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 10/16/2021
 • E-mail : info@dce-et.com
 • Phone Number : 0114403434
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/04/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCE/BM/114/2021

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለወንጪ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት በግብዓትነት የሚውል የባለ 32 ጌጅ ኮርጌትድ ቆርቆሮ ዕቃው ግምዣ ቤት (stock) ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

No Description Item specification Unit Qty
1 Corrugated iron Sheet 32 gage Pcs 1,760

 ስለሆነም፡-

 1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፣ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችላቸው የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት፡
 3. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ኦርጅናል ወይም የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት ኮፒ ካታሎግ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ወይም በጨረታ መክፈቻ ቀን በካታሎጉ ላይ የሚወዳደሩበትን ዕቃ ለይቶ በማመልከት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በአንድ ዓይነት ሞዴል ብቻ ነው፡፡ በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሠፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መ/ቤት የግዥ የሥራ ሂደት ኬዝ ቲም ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
 6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታው ለተዘረዘሩት ዕቃዎች ብዛት (Quantity) በሙሉ መሆን አለበት፡፡
 7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እሰከ ጥቅምት 24/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 8. ጨረታው ጥቅምት 24/2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
 9. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡– የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34/33

ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72

ፖሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46

ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ

WWW.dce-et.com/Email:-info@dce-et.com