ዲ.ኤም.ሲ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.ግ.ማህበር የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎችን ፣ የፕሪንተር እና የኮፒ ማሽን ቀለሞችን እንዲሁም የፅዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Office Items & Equipment Supplies
 • Posted Date : 10/16/2021
 • Phone Number : 0114199273
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/23/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ዲ.ኤም.ሲ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.ግ.ማህበር የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎችን ፣ የፕሪንተር እና የኮፒ ማሽን ቀለሞችን እንዲሁም የፅዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

 1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪ በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች በዲ.ኤም.ሲ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ማህበር ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ጧት ከ2፡00-6፡00 እና ከሰዓት ከ7፡00-11፡00 ድረስ የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ) በመክፍል መውሰድ ይችላሉ እንዲሁም ጨረታው ጥቅምት 8 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ክፍት ሆኑ እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት ከዚህ በታች አድራሻ ይከፈታል፡፡
 5. ተጫራቾች በጨረታው ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ፣ሙሉ አድራሻቸውን፣ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስፈር አለባቸው፡፡
 6. ድርጅቱ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡-ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ለቡ መብራት ኃይል

         ከሳሙኤል ህንፃ ፊት ለፊት ካለው ዋናው መስሪያ ቤት 9ፎቅ

ስልክቁጥር፡ 011 41 99 273

አዲስ አበባ

ዲ.ኤም.ሲ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ማህበረ