የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኙ የሆቴል መስተንግዶና ተያያዥ አገልግሎቶች የሚሰጡ ድርጅቶችን አወዳድሮ የሆቴል አገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም

Overview

 • Category : Catering Service
 • Posted Date : 10/19/2021
 • Phone Number : 0944309492
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/29/2021

Description

የሆቴል መስተንግዶና ተያያዥ አገልግሎቶች የጨረታ ማስታወቂያ

ኢሰመኮ/ብ/ግ/ጨ/001/2014

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በፌደራል ሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 55/14 መሰረት በአዋጅ ቁጥር 210/1992 (በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው) ነጻ ፌደራላዊ መንግስት አካል ሆኖ የተቋቋመና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ የሆነ ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት፣ መከበርና እና ጥበቃ የሚሰራ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋም ነው፡፡ ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኙ የሆቴል መስተንግዶና ተያያዥ አገልግሎቶች የሚሰጡ ድርጅቶችን አወዳድሮ የሆቴል አገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም

አገልግሎቱ የሚያስፈልግባቸው ከተሞች አዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ

 • ቢያንስ 30 ማረፊያ ክፍሎች ያሉት
 • የስብሰባ አዳራሾች ያሉት(አንድ 150 ሰዎችን የሚይዝ ሁለት 50 ሰዎች የሚይዙ)
 • ምሳ፣
 • ሪፍሬሽመንት ½ ሊትር የማዕድን ውኃን ጨምሮ (በቀን 2 ጊዜ ወይም አንድ ጊዜ)
 • ፊሊፕ ቻርት፣ ማስታወሻ ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ ማርከር ማስክና ሳኒታይዘር ማቅረብ የሚችል

ለአዲስ አበባ ሁለት ሆቴሎች በአሸናፊነት የሚመረጡ ሲሆን እነዚህም፡-

ባለ አራት ኮከብ ሆቴል (አንድ አሸናፊ ሆቴል የሚመረጥ እንዲሁም)

ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል (አንድ አሸናፊ ሆቴል የሚመረጥ ይሆናል)

ለአዲስ አበባ(በኢሰመኮ ዋና መ/ቤት የምግብ አዳራሽ) የሚቀርብ

 • ምሳ እስከ 150 ለሚሆኑ የኮሚሽኑ ሰራተኞች (ከሰኞ እስከ ዓርብ) ከ6፡30 እስከ 8፡00 ሰዓት የበዓላት ቀናትን ሳይጨምር
 • ውኃ እና ለስላሳ መጠጦች ማቅረብ የሚችል

በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱት መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

 • ቢያንስ ከሁለት ዓመት ላላነሰ ጊዜ በዘርፉ ወይም በአገልግሎቱ የሥራ ልምድ ያለው እንዲሁም ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ የሀገር ውስጥና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተመሳሳይ አቅርቦት የመስጠት ልምድ ያለውና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
 • በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸው የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት እና በአቅራቢነት(Supplier List) የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን በተለያየ ፖስታ አሽገውና ማህተም አድርገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ጨረታው ጥቅምት 19 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 • ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን

አድራሻችን፡- ቦሌ ፍላሚንጎ ፊትለፊት ሐያት ሪጀንሲ ሆቴል አጠገብ አዲሱ ሰንሻይን ህንጻ

 ስልክ ቁጥር 0944309492 ወይም 0911537381