ኦቪድ ኮንስትራክሽን ኃ/ተ/የግ/ማህበር በአሮሚያ ብ/ክ/መ በገላን ከተማ በሚገኘው የድርጅታችን መጋዘን ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ንብረቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መመሪያ መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Ovid-Trading-ethiopia-logo

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 10/19/2021
 • Phone Number : 0911247319
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/26/2021

Description

 የጨረታ  ማስታወቂያ

ድርጅታችን ኦቪድ ኮንስትራክሽን ኃ/ተ/የግ/ማህበር በአሮሚያ ብ/ክ/መ በገላን ከተማ በሚገኘው የድርጅታችን መጋዘን ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ንብረቶች (የመፀዳጃ ቤት የግንባታ እቃዎች፤ ልዩ ልዩ ማሽኖች፤ የህንፃ መሳሪያዎች እና የቢሮ  የኤሌክትሮኒክስ መገልያ እቃዎች) ከዚህ  በታች  በተዘረዘረው መመሪያ መሰረት በግልፅ ጨረታ  አወዳደሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 1. ተጫራቾች በድርጅታችን መጋዘን ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ ለማየት ከፈለጉ መጋዘኑ በሚገኝበት በአሮሚያ ብ/ክ/መ በ ገላን ኢንደስትሪ ዞን ፤ጎጌቻ ቀበሌ፤ አቃቂ ወረዳ፤  በመገኘት 300 እስ1100 ጥቅምት 11, 2014 እስከ ጥቅምት16, 2014 መመልከት ይችላሉ፡፡
 2. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ያቀረበውን የጨረታ ዋጋ በመግለጽ የጨረታ ማስከበሪያ በተጫረተው ዋጋ ላይ  የ 5 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ  በ ኦቪድ  ኮንስትራክሽን ኃ/ተ/የግ/ማህበር ስም በማያያዝ ከ ጥቅምት 11, 2014 እስከ ጥቅምት 16, 2014 ድረስ  300 እስ1100 የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በዋናው መ/ቤት ቦሌ ክ/ከ ወረዳ 03 የቤ.ቁ  አዲስ  ፤ 22 ጎላጉል  ወደ  አደይ  አበባ  እስቴድየም በሚወስደው መንገድ ላይ  ወርቁ  ህንፃ  ጀርባ  ኦቪድ  ግሩፕ  ህንፃ  4ተኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
 3. በጨረታ ለተሸነፉት ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል፡፡ ለጨረታው አሸናፊዎች ደግሞ ያሰያዙት ገንዘብ ለሚገዙት ዕቃ ከሚከፍሉት ዋጋ ይታሰብላቸዋል፡፡
 4. አሸናፊዎች በጨረታ ላሸነፉት የተለያዩ ንብረቶች ቀሪውን ክፍያ  እና 15 በመቶ የእሴት ታክስ  አክለው በመክፈል የጨረታው ውጤት ከተገለጸበት ጊዜ  ጀምሮ ባሉት  5 የስራ ቀናት  ውስጥ ዕቃዎችን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ  ገደብ  ያሸነፉትን ንብረት ከፍለው ካልወሰዱ ኩባንያው አሸናፊውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ከመሆኑም በላይ  ለጨረታ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ አይሆንም፡፡
 5. ድርጅታችንም ዕቃውን ጨረታ  በማውጣትም ሆነ ያለጨረታ የመሸጥ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 6. ጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ  የተጨማሪ እሴት  ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን በግልጽ  ሁኔታ  በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ  ላይ ካልገለጹ  በስተቀር ባቀረቡበት ዋጋ ላይ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት  ታክስ  ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል፡፡
 7. የተለያዩ ንብረቶች በጨረታ እስከ ተሸጡበት ጊዜ ድረስ የሚፈለግ ግብርና ታክስ  ወይም ሌላ ክፍያ ቢኖር  የሻጭ ኃላፊነት ይሆናል፡፡
 8. አሸናፊ ተጫራቾች የገዙትን የተለያዩ ንብረቶች ከቦታው ላይ በራሳቸው ወጪ አንስተው ይወስዳሉ፡፡
 9. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ፡፡
 10. ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ የዋጋ ማስተካከያ ወይም ስርዝ ድልዝ ካደረጉ በተስተካከለው ፊት ለፊት  መፈረም አለበት ፡፡
 11. የጨረታ ሰነዱን ከዋናው መ/ቤት ወይንም በአሮሚያ ብ/ክ/መ በገላን ከተማ በሚገኘው የድርጅታችን መጋዘን መውሰድ ይቻላል ፡፡ የመጫረቻ ዋጋ በእርሳስ መሙላት አይቻልም፡፡
 12. አንድ ተጫራች ከአንድ ጊዜ በላይ የጨረታ ሰነድ ማሰገባት አይችልም ፡፡
 13. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ ፊርማ ከሌለበት የጨረታው ሰነድ ዋጋ አይኖረውም፡፡
 14. በጨረታ ሰነድ ላይ ስም ፊርማ እንዲሁም ስልክ ቁጥር መፃፍ ይኖርበታል፡፡
 15. ጨረታው ጥቅምት 16, 2014 .ም በ1100 በስራ ሰዓት ተዘግቶ ውጤት በ 3 ቀን ውስጥ ይገለጻል፡፡ ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ዲስ በባ: Tel: 0911-24-73-19 /   0920349779 /  0911483102  / 0919366175                        

     ገላን (ዱከ): 0913860735/0905-13-47-65