በኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት የቤተ ክርስቲያኗ ንብረት የሆነው ለንግድ አገልግሎት የሚውል ቤት በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : House & Building Rent
 • Posted Date : 10/19/2021
 • Phone Number : 0111566378
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/02/2021

Description

የንግድ ቤት ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

 1. በኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት የቤተ ክርስቲያኗ ንብረት የሆነው ለንግድ አገልግሎት የሚውል ቤት በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
 2. የድርጅቱ አድራሻ፡- በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዐ1 የቤት ቁጥር 71ዐ/33 ባንኮ ዲሮማ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲጠቀምበት የነበረው፣
 3. ድርጅቱ ለኪራይ ያቀረበውን ለቢሮ በጨረታ ተወዳድሮ ለመከራየት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 1ዐ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡3ዐ እስከ 10፡ዐዐ ክፍሎቹን በአካል ቀርቦ በማየት ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር2ዐዐ.ዐዐ(ሁለት መቶ ብር) ከፍሎ ገዝቶ የሚከራይበትን የኪራይ ዋጋ መጠንና አስፈላጊ መረጃዎችን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በድርጅቱ ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
 4. ተጫራቾች ነጋዴ ከሆኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ደረሰኝ፣ ኢንቨስተር ከሆነ የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣ የንግድ ማኅበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሑፍ፣ የሙያ አገልግሎት ሰጪ ከሆነ የሙያ ፈቃዱን ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
 5. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ቤት ከሚሰጡት የመጀመሪያ ወርሃዊ የኪራይ ጠቅላላ ዋጋ 15% (አሥራ አምስት በመቶ)የሚሆነውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ(CPO) ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ዋናውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ጨረታው በ1ዐኛው ቀን ከቀኑ 1ዐ፡ዐዐ ተዘግቶ በማግስቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ከጠዋቱ በ3፡ዐዐ ሰዓት በድርጅቱ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
 7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

    ለበለጠ መረጃ

 በስ.ቁ. ዐ111 56 63 78 ወይም

በድርጅቱ ጽ/ቤት በአካል ቀርበው ይጠይቁ፡፡