የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር (EVA) ከአውሮፓ ሕብረት (EU) ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በሶስት ብሔራዊ ክልሎች (አማራ፣ ኦሮሚያ እና ሶማሌ) የካቴሪንግ (Catering) አገልግሎት (Refreshment and Lunch/First grade Buffet) መስጠት የሚችሉ ሆቴሎችን በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል።

Overview

 • Category : Catering Service
 • Posted Date : 10/20/2021
 • Phone Number : 0115525020
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/27/2021

Description

የሆቴል አገልግሎት ለማግኘት የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር (EVA) ከአውሮፓ ሕብረት (EU) ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በሶስት ብሔራዊ ክልሎች (አማራ፣ ኦሮሚያ እና ሶማሌ) የእንስሳት ሀብት ልማት ፕሮግራሞችን ለማጎልበትና የዘርፉን ምርታማነት ይበልጥ ለማሻሻል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

ማኅበሩ የእንስሳት ልማት ሥራዎችን ለማስፋፋት፣ እንዲሁም ጠቃሚ ልምዶችንና ምርጥ ተሞክሮዎችን ለማስተዋወቅ የሚያስችል 35ኛ ጠቅላላ ዓመታዊ ኮንፈረንስ በሕዳር 8-9/2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስና ኮምፒውቴሽናል ኮሌጅ (Arat Kilo Campus) ውስጥ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁም መሠረት የኮሮና በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ መርሆችን በተከተለ  መልኩ ለኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች የካቴሪንግ (Catering) አገልግሎት (Refreshment and Lunch/First grade Buffet) መስጠት የሚችሉ ሆቴሎችን በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ሆቴሎች እንዲወዳደሩ በአክብሮት ይጋብዛል፡-

 1. የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድና የ2013 ዓ.ም. ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፣
 2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክርነት ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
 3. በመንግስት ግዢ፣ ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የካቴሪንግ አገልግሎት ለመስጠት መመዝገባቸውን የሚያረጋገጥ ሕጋዊ ሰነድ ማቅረብ የሚችል፣
 4. የCOVID-19 ፕሮቶኮልን ተመርኩዞ በአንድ ጊዜ ቢያንስ 350 ተሳታፊዎችን ማስተናገድ የሚችል ድንኳን፣ የመመገቢያ ጠረጴዛ እና ወንበሮችን በኮንፈረንሱ ሥፍራ አቅራቢያ ማሰናዳት የሚችሉ፣
 5. ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተዘረዘሩ መሥፈርቶችን የሚያሟሉ ሆቴሎች የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ ቀናት በማኅበሩ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 303/306 ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2:30 እስከ 10:30 ድረስ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
 6. ተጫራቾች ማህበሩ ባቀረበው የዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ በተገለጸው ዝርዝር (Specification) መሠረት ዋጋቸውን ከVAT በፊት እና በኋላ በግልጽ ሞልተው ሰንዱንም ኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ ለድርጅቱ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% (በአማካይ 350 ሰው በቀን ሆኖ ለ2 ቀናት አገልግሎት) በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፣ ጨረታውን ያላሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት ገንዘብ አሸናፊ ድርጅት እንደተለየ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
 8. ጨረታው በ8ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል። ሆኖም የተጫራቾች ወይም የወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
 9. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር +251-115-525-020፣ 09-11-18-05-33፣ 09-60-03-71-25፣ 09-52-67-77-94 ወይም 09-40-08-61-94 ደውሎ ዝርዝር መረጃ መጠየቅ ይቻላል።

የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማህበር