የፌዴራል የሥነምግባር አና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የህትመት አገልግሎት ግዥ

Overview

 • Category : Printing & Publishing Service
 • Posted Date : 10/20/2021
 • Phone Number : 0115536907
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/01/2021

Description

የፌዴራል የሥነምግባር አና ፀረሙስና ኮሚሽን

የህትመት አገልግሎት ግዥ

ግልጽ ጨረታ ቁጥር 002/2014

ተ.ቁ የሚገዛው ዕቃ ወይም የዓገልግሎት ዓይነት የግዥዉ ምድብ የጨረታው መለያ ቁጥር ግዥዉ የሚፈጸምበት የገንዘብ ምንጭ   የጨረታው
ማስከበሪያ
/ዋስትና/
በኢት ብር
ተጫራቾች ማቅረብ የሚገባቸው
የመወዳደሪያ ሃሳብ
የጨረታው  ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ለመጀመሪያ ጊዜ በወጣ   የጨረታው  መክፈቻ
ጊዜ ይህ ማስታወቂያ
 ለመጀመሪያ ጊዜ በወጣ
ከመንግስት ግምጃ ቤት ከእርዳታ ቀን ሰዓት ቀን ሰዓት
1 የህትመት አገልግሎት ግዥ አገልግሎት ግዥ 002/2014  √   10,000.00 የዋጋ እና የቴክኒክ ሰነድ በሁለት የተለያዩ
ኤንቨሎፖች
በ16ኛው  ቀን 8:00 በ16ኛው  ቀን 8፡15

ተጫራቾች ከላይ የተገለፀውን ጨረታ ለመሳተፍ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሕጋዊ ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ኮፒ፣ የስልክ ቁጥር  011 5 53 69 07 / 011 5 58 07 43
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ኮፒ፣ የፖ.ሳ.ቁ 34798/34799
  3. በመንግስት የዕቃ/የአገልግሎት ግዥ ላይ በአቅራቢነት ለመሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ ሠርተፍኬት ኮፒ ወይም በድረ ገጽ የተመዘገቡበት ማስረጃ ሰነድ፣ የፌዴራል የሥነምግባር አና ፀረ ሙስና ኮሚሽን
  4. የጨረታ ማስከበሪያ 10,000/አስር ሺህ ብር/ በሲፒኦ ወይም በኮሚሽኑ 4ኛ ፎቅ ከሚገኘው ቢሮ ቁጥር 403 በጥሬ ገንዘብ ገቢ ያደረጉበት ደረሰኝ፣
  5. በኮሚሽኑ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ/ ብቻ በመክፈል  የጨረታውን ሰነድ በመግዛት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የሚገኙትን ምዕራፍ 1 ክፍል 4 የጨረታ ማቅረቢያ እና የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል መግቢያ ቅፆችን እንዲሁም በምእራፍ 2 ክፍል 6 የተቀመጠውን Compliance sheet በመሙላት፣
  6. በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 7 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ከቴክኒክ የመወዳደሪያ ሐሳብ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች አመች ሆኖ ባገኙት የድርጅታቸው ሰነድ ላይ የቴክኒክ መወዳደሪያ ሃሳብ / Technical proposal/  እና የዋጋ ማቅረቢያቸውን /Financial Proposal/  ሞልተው በመፈረም እና ማኅተም በማድረግ በተለያዩ ኤንቨሎፖች አሽገው በኤንቨሎፖቹ የጀርባ ገጽ ላይ የግዥውን ዓይነት በመጥቀስ፣ ቴክኒካል ፕሮፖዛል /Technical proposal/  እና የዋጋ ማቅረቢያ /Financial Proposal/ ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶች በማለት በጉልህ በመፃፍና ከኤንቨሎፑ ፊት ለፊት የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተገለፀው የመጨረሻ የጨረታ ማቅረቢያ ጊዜ ድረስ  ባሉት ተከታታይ ቀናት ውስጥ የዋጋ ማቅረቢያቸውን /Financial Proposal/ እና የቴክኒክ መወዳደሪያ ሃሳባቸውን / Technical proposal/ የያዙ ኤንቨሎፖችን ለፌዴራል የስነምግባር እና የፀረሙስና ኮሚሽን 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403  ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  9. የጨረታው ሳጥን ከላይ በተገለጸው የጨረታው የመጨረሻ ማቅረቢያ ቀን እና ሰዓት ላይ ተዘግቶ በእለቱ ከላይ በተገለጸው የመክፈቻ ቀንና  ሰዓት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመክፈቻ ስነስርዓት ይካሄዳል፡፡
  10. ከላይ የተገለጸው የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን  የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚዘጋና በዕለቱ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. በጨረታው መክፈቻ ቀን የቴክኒክ መወዳደሪያ ሀሳብ ብቻ ይከፈታል፡፡ የዋጋ ማወዳደሪያ ሃሳበ ኤንቨሎፖች የሚከፈቱት በቴክኒክ ብቁ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች ብቻ ሲሆን የቴክኒክ ገምገማ ውጤቱን ለሁሉም ተጫራቾች በእኩል ጊዜ እንዲያውቁት ይደረጋል፡፡
  12. ኮሚሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 የፌዴራል የሥነምግባር አና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን