አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ በግጭትና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸው ለደንበኞቸ የካሣ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችን እና የተለወጡ አሮጌ የተሽከርካሪ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 10/21/2021
 • Phone Number : 0116637716
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/11/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ በግጭትና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸው ለደንበኞቸ የካሣ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችን እና የተለወጡ አሮጌ የተሽከርካሪ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 1. የመኪኖቹን/ንብረቶቹን ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች እስከ ረቡዕ ህዳር 1 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ ተሸከርካሪዎቹን በስራ ሰዓት ማየት የሚችሉ ሲሆን ተሸከርካሪዎቹ የሚገኙበት አድራሻ ፡-
  • በአፍሪካ ኢንሹራንስ ጉዳት የደረሰባቸው ተሽከርካሪዎች ማቆሚያ ቦታ ቃሊቲ ማደያ በሚ­ ተርሚናል ወደ ውስጥ5 ኪ.ሜ ገባ ብሎ የተጎዱ መኪኖች ማቆያ ቅጥር ግቢ ፣ እና
  • ጎንደር ቅርንጫፍ
 2. ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውንና የተሽከርካሪዎቹን/ንብረት ዝርዝር የያዘውን ፎርም ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቦሌ ሩዋንዳ አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ ሕንፃ በሚገኘው በኩባንያው ዋናው መ/ቤት ወይም ከላይ በተራ ቁጥር 1.1 ላይ በተገለፀው ስፍራ በመገኘት እስከ ረቡዕ ህዳር 1 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ የማይመለስ 50 ብር በመክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡Ý
 3. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን የእያንዳንዱን ተሽከርካሪ/ንብረት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ረቡዕ ህዳር 1 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ  ቦሌ ሩዋንዳ በሚገኘው በኩባንያው ዋና መ/ቤት ካሣ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ/ንብረት የመነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ(P.O.) ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን ይህን መስፈርት የማያሟላ ተጫራች ወዲያውኑ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡ ተጫራቹ በጨረታው ከተሸነፈ በማስያዣ ያስያዘው ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆንለታል፡Ý
 5. ጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ የሚጫረቱበት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት፡፡
  • ጨረታው ሐሙስ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ጥዋቱ 3 ሰዓት ቦሌ ሩዋንዳ በአፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ ዋናው መ/ቤት  ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል፡Ý
 6. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪ/ንብረት ሙሉ ክፍያ 15% VAT ጨምሮ በ 7 የሥራ ቀናት ውስጥ በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ለአስር ቀናት በየቀኑ 100.00 (መቶ ብር) የማቆሚያ ቦታ ኪራይ የምናስከፍል ሲሆን በ10 ቀናት ውስጥ ካላነሱ ግን ያስያዙት ገንዘብ በቅጣት መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል፡”
 7. ለጨረታ በቀረቡት ተሽከርካሪዎችና ንብረቶች ላይ የሚፈለጉ የስም ማዛወሪያ፣ ፣ ግብርና ልዩ ልዩ ወጪዎች ቢኖሩ በጨረታው አሸናፊ የሚከፈሉ ይሆናሉ፡፡
 8. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡”
 9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116-63-77-16/19 እንዲሁም ለመቀሌ ተጫራቾች በስልክ ቁጥር 0344-40-19-32 በመደወል ወይንም በኩባንያው ዋና መ/ቤት በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡”

ማሳሰቢያ፡ ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን እንዳለበት መሆኑን እንገልፃለን