ትራኮን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጀሞ 1 ሆፕ ዩኒቨርስቲ ጀርባ እያስገነባ ለሚገኘው 3B+G+22 ሁለት መንትያ የአፓርታማ ህንጻዎች ግልጋሎት የሚውል የኤሌክትሪክ ገመድ እና ደረቅ ኮንዲውት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Tracon-Trading-Logo-1

Overview

  • Category : Construction Raw Materials
  • Posted Date : 10/22/2021
  • Phone Number : 0913098889
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 11/06/2021

Description

ትራኮን ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግል ማህበር

ለትራኮን ሪል ስቴት የኤሌክትሪክ ገመድ እና ኮንዲውት ግዥ ለመፈፀም  የወጣ ግልፅ ጨረታ

ድርጅታችን ትራኮን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጀሞ 1 ሆፕ ዩኒቨርስቲ ጀርባ እያስገነባ ለሚገኘው 3B+G+22 ሁለት መንትያ የአፓርታማ ህንጻዎች ግልጋሎት የሚውል የኤሌክትሪክ ገመድ እና ደረቅ ኮንዲውት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ጥራቱን የጠበቀ የኤሌክትሪክ ገመድ/single core semi flexible electric wire/ እና ደረቅ ኮንዲውት/Rigid conduit/በማቅረብ ልምድ ያላችሁ አምራችና አቅራቢዎች የጨረታ ሰነዱን ትራኮን ታወር 1ኛ ፎቅ ከሚገኘው ቢሮ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የማቴሪያሎቹን ስፔሲፊኬሽን፤ናሙና እና ሌሎች የጥራት ማረጋገጫ ማስረጃዎችን ያካተተ የቴክኒካል ዶክመንት በአንድ የታሸገ ፖስታ፤እንዲሁም ለፋይናንሻል ውድድር የጨረታ ሰነዱን በመሙላት እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/BID BOND/በማካተት በተለየ ፖስታ በማድረግ ይህ ጨረታ በመጀመሪያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ቡኃላ ባሉት 10/አስር/ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ እንዲያስገቡ ይጠበቃል፡፡

ጨረታው ዓርብ ጥቅምት 26/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ  በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡

ተጫራቾች የሚከተሉትን መመዘኛዎች እንዲያሟሉ ይጠበቃል፡-

  1. የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፍቃድ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
  2. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አነድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ያቀረቡትን ዋጋ 2 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. የተሟላ የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንቶች አስከ ጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ በትራኮን ታወር 1ኛ ፎቅ ማስገባት የሚቻል ሲሆን፤ጨረታው የሚከፈተው ጀሞ/ለቡ በሚገኘው የትራኮን ሪል ስቴት ፕሮጀክት ቅጥር ግቢ ይሆናል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ጥቁር አንበሳ-ትራኮን ታወር 1ኛ ፎቅ  –  ስልክ፡-0913098889/0989098625

Send me an email when this category has been updated