በአምቦ ማዕድን ውሃ አክሲዮን ማኅበር የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል ።

Ambo-Mineral-Water-S.c.-Logo

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 10/26/2021
 • Phone Number : 0911939397
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/04/2021

Description

 በድጋሚ የወጣ ግልፅ የመኪና ጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን በአምቦ ማዕድን ውሃ አክሲዮን ማኅበር የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል ። የተሽከርካሪዎቹ መገኛ ቦታ በቃሊቲ ዋና መስሪያ ቤት ማለትም ከአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም አቅራቢያ ይገኛል። ተጫራቾች ንብረቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአ. ማ ዋና መ/ቤት በአካል ተገኝተው ንብረቱን መመልከት ይችላሉ:

ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ አመልካቾች በዚህ ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

 1. ተጫራቾች የተሽከርካሪዎችን ዝርዝር ከፋይናንስ ክፍል የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ማግኘት ይችላሉ ፡፡
 2. ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር በመያዝ በጨረታ መክፈቻ ቀን ይዘው በማቅረብ መወዳደር ይጠበቅባቸዋል ።
 3. ሲፒኦ በአምቦ ማዕድን ውሃ አክሲዮን ማኅበሩ ስም ብቻ መዘጋጀት አለበት ።
 4. ተጫራቾች ለተጫረቱት ዋጋ ቫትን አካቶ ማቅረብ አለባቸው ካልተገለፀ ግን የቀረበው ዋጋ ቫትን ጨምሮ አንደተሰጠ ይቆጠራል ፡፡
 5. የጨረታ መክፈቻ ቀን ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ህዳር (November) 04 2021 እአአ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይጀመራል ፡፡ ጨረታውም በግልፅና በቀጥታ ይካሄዳል ።
 6. አሸናፊነቱ የተረጋገጠ ተጫራች የአሸነፈበትን የተሽከርካሪ ዋጋ በሁለት ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል ፡፡
 7. አሸናፊው የተሽከርካሪውን ዋጋ ጥሬ ገንዘብ ካስገባ በኋላ በ7 /ሰባት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተሽከርከሪውን ማንሳት አለበት ፡፡ በአሸናፊው ተሽከርካሪው ካልተነሳ አሸናፊው ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ለእያንዳንዱ ቀን ብር 1000 ይከፍላል ፡፡
 8. አሸናፊው በሁለት ቀናት ውስጥ ጥሬ ገንዘብ ካላስቀመጠ በዋስትና የተያዘው ሲፒኦ ወደ አምቦ ማዕድን ውሃ አክሲዮን ማህበር በማሰተላለፍ እንዳልተጫረተ ይቆጠርና ጨረታው ይሰረዛል ፡፡
 9. ከባለቤትነት ማስተላለፍ ጋር የተያያዙ ሁሉም ክፍያዎች በአሸናፊው ተጫራች ይሸፈናል።
 10. አምቦ ማዕድን ውሃ አ.ማ ተሽከርካሪው ከአምቦ ግቢ ከመውጣቱ በፊት ላለው ለማንኛውም የህግ እና ተያያዥ ጉዳዮች ኃላፊነቱን ይወስዳል ፡፡
 11. ከላይ ያሉትን ማናቸውንም መስፈርቶች አለመሟላት ከጨረታው ውድቅ ያስደርጋል ፡፡

መስፈርቶቹን የሚያሟሉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃዎችን ከድርጅቱ ክፍል በሚከተለው ቁጥር ማግኘት ይችላሉ ወይም 0911939397 በአካል በመገኘት መረዳት አንደሚችሉ አናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ፡-አክስዮን ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

Send me an email when this category has been updated