የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አ.ማ. የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ጥሪ

Announcement
yetebaberut-Beherawi-logo

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 10/27/2021
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/08/2021

Description

የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አ.ማ.

የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ጥሪ

የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አ.ማ. የማህበሩ ዋና ገንዘብ ብር 244,035,000.00 የምዝገባ ቁጥር MT/AA/3/0006398/2004  ዋና መስሪያ ቤት አዲስ አበባ የባለአክሲዮኖች 17ተኛ መደበኛ እና 9 ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ህዳር 9 ቀን 2ዐ14 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡3ዐ ሰዓት ጀምሮ በሒልተን  ሆቴል ይካሄዳል፡፡

ስለሆነም የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ተወካዮቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን፣ ቦታና ሰዓት በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የባለአክሲዮኖች 17ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳ

 1. የጉባዔውን አጀንዳ ማጽደቅ፣
 2. የ2020/2021 በጀት ዓመት የዲሬክተሮች ቦርድን የሥራ ክንውን ሪፖርት ማድመጥ፣
 3. የ2020/2021 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማድመጥ፣
 4. ከላይ በተራ ቁጥር 2 እና 3 በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
 5. በዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደል (አከፋፈል) ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
 6. የ2021/2022 በጀት ዓመት የውጪ ኦዲተሮችን መምረጥና ክፍያቸውን መወሰን፣
 7. የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ ትራንስፖርት አበልን መወሰን፣
 8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ መምረጥ፣
 9. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ማካሄድ፣
 1. የጉባዔውን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ፣

የባለአክሲዮኖች 9 ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳ

 1. የጉባዔውን አጀንዳ ማጽደቅ፣
 2. አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፣ የተደረጉ የአክሲዮን ግዢ እና ዝዉውሮችን እንዲሁም በውርስ የተላለፉ አክሲዮኖችን ማሳወቅ፣
 3. የኩባንያውን መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻል፣
 4.   የዕለቱን ጉባዔ ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ፣

ማሳሰቢያ

  1. በጉባዔው ላይ ለመገኘት የማይችሉ ከሆነ ሌላ ሰው መወከል የሚችሉ ሲሆን ውክልናውም፣

ሀ.    ከሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ የተረጋገጠ ወይንም

ለ.    ጉባዔው ከመደረጉ ሦስት /3/ ቀናት በፊት ባለአክሲዮኑ ራሣቸው በአካል ቀርበው ከማህበሩ የውስጥ ኦዲተር ፊት በመፈረም በሰነድ የተረጋገጠ ውክልና በመስጠት መሆን ይኖርበታል፡፡

  1. ውክልና ለመስጠትም ሆነ በጉባዔው ለመሣተፍ የሚመጡ ሁሉም ባለአክሲዮች ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ወይም መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አ.ማ.  የዳይሬክተሮች ቦርድ

Send me an email when this category has been updated