ዓባይ የህትመትና የወረቀት ፓኬጅንግ ፋብሪካ ለፋብሪካዉ አገልግሎት የሚሆኑ Print Management Information System (IPMIS), Print Cost Estimation System በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈለጋል፡፡

abay-printing-and-paper-packaging-factory-logo

Overview

 • Category : Machinery
 • Posted Date : 10/29/2021
 • Phone Number : 0583218865
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/20/2021

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር አሕየወፓ-04/02/2014

ዓባይ የህትመትና የወረቀት ፓኬጅንግ ፋብሪካ ለፋብሪካዉ አገልግሎት የሚሆኑ

ሎት1 Supply, Installation, and Implementation of Integrated Print Management Information System (IPMIS)

ሎት 2 Supply, Installation, and Implementation of Print Cost Estimation System.

በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈለጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታዉ እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

 1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የፀና የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸዉ
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸዉ
 3. 200,000.00(ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ  (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ተራ ቁጥር  1-3 የተጠቀሱትንና  የሚመለክታቸዉን  ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
 5. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ፤የተጫራቾች መመሪያ፤የዉል ረቂቅ፤የዋጋ መሙያ ፎርምና ቴክኒክ መግለጫ ያያዘዉን የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዓባይ ሕትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ  ኃ/የተ/የግ/ማ   ባህርዳር  ከተማ  አባይ ማዶ ኢንዱስትሪ መንደር ከጣና ሞባይል አከባቢ ከሚገኘዉ ከፋብሪካዉ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ወይም አዲስ አበባ 4 ኪሎ አማራ ልማት ማህበር አዲሱ ሀንፃ  ምድር ላይ ቢሮ ቁጥር 6 ከሚገኘዉ ከፋብሪካዉ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ጽ/ቤት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000281546078 ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን የባንክ ደረሰኝ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
 6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ተጨማሪ እሴት ታከስን ጨምሮ የጠቅላላ ዋጋዉን 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድረገዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
 7. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሂሳቡን የቴክኒካልና የፋይናንሻል ጨረታዉን ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከፋብሪካዉ አቅርቦትና ሎጅስቲክስ መምሪያ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ  ኅዳር 10 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ እና የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ እስከ 60 (ስልሳ) ቀናት ድረስ ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡እንዲሁም የጨረታ ዋጋ በዉል ዘመኑ በሙሉ የፀና መሆን አለበት::
 9. ማንኛዉም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክስ  ዋጋ ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
 10. ቴክኒካል ጨረታ ብቻ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከፋብሪካዉ ግቢ ከአቅርቦትና ሎጅስቲክስ መምሪያ ኅዳር 10 ቀን 2014 ዓ/ም በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ስዓት ይከፈታል፡፡የፋይናንሻል ጨረታ የሚከፈተበት ቀን  የቴክኒካል ጨረታ ላለፉት ብቻ በዉስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
 11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
 12. በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታዉ ዝረዝር መረጃ ከፈለጉ ከፋብሪካዉ አቅርቦትና ሎጅስቲክስ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ  ቁጥር 0583218865/0911346566 በመደወል  ማግኘት ይቻላል፡፡

ዓባይ ሕትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ባህር ዳር