ሕብረት ባንክ አ.ማ. በዑራኤል እና ቀበና ቅርንጫፎች በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዛቸዉንና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡

hibret-bank-done-logo-reportertenders-5

Overview

 • Category : House & Building Foreclosure
 • Posted Date : 10/29/2021
 • Phone Number : 0115549963
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/08/2021

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ፤

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በዑራኤል እና  ቀበና ቅርንጫፎች በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዛቸዉንና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡

ተ.ቁ የቅርንጫፍ ስም የተበዳሪ ስም የአስያዥ ስም ቤቶቹ የሚገኝበት አድራሻና የቦታዉ ስፋት የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥር የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
1 ዑራኤል ሙኡዝ ተካ አብርሃ ወ/ሮ ሮማን ሃ/ስላሴ ለሚኩራ ክ/ከተማ (በድሮው የካ ክ/ከተማ ወረዳ 13) ፣ የቦታ ስፋት 153 ካ.ሜ የሆነ የመኖሪያ ቤት የካ/195563/08 4,762,353.00 ህዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
2  ቀበና አስራት ጌዲዮን ሽፈራው እነ አስራት ጌዲዮን አ.አ ከተማ፣ጉለሌ ክ/ከ ወረዳ 9 የሚገኝ፣ የቦታው ስፋት 199 ካ.ሜ የሆነ የመኖሪያ ቤት  

9/5/378850/04

 

2,485,478.00

ታህሳስ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት

     የሐራጅ ደንቦች

 1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
 2. አሸናፊ የሆነዉ ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት (15) ቀናት ዉስጥ አጠቃልሎ ካልከፈለ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሀራጅ ሲቀርብ ለሚታየዉ የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
 3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪዎች እና አስያዦች ብቻ ናቸዉ፡፡
 4. የሐራጅ ሽያጩ የሚካሄደዉ የመያዣዉ ንብረት በሚገኝበት ቦታ ላይ ነዉ፡፡
 5. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ በሐራጁ ሰላሳ (30) ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም፡፡
 6. የጨረታው አሸናፊ ንብረቱ ያለበትን የሊዝ እዳ ሙሉ በሙሉ ከፍሎ ስም ለማዛወር ፍቃደኛ የሆነ መሆን አለበት፡፡
 7. ለሐራጅ የቀረበዉን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልጉ ከአበዳረው ቅርንጫፍ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታዉ ቀን ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
 8. የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸዉ በህግ የተወሰኑ የታክስና ግብር የስም ማዛወሪያ ጭምር /የጨረታዉ አሸናፊ/ ገዥዉ ይከፍላል፡፡
 9. ባንኩ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
 10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 554 99 63/97 89/ 95 11 ዑራኤል ቅርንጫፍ እና 011 1 24 65 10/11/12 ቀበና ቅርንጫፍ ወይም 0114-70-03-15/69/47 ሕግ አገልግሎት መምሪያ ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡