ግሎባል ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መሥሪያ ቤቱ የሚገኘበትን ህንፃ አጠቃላይ የውጭ ግድግዳ እና መስታወት ለማፀዳት አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶችን በማወዳደር ለማሠራት ይፈልጋል።

Global-Insurance-Company-S.C-logo-reportertenders

Overview

  • Category : Cleaning & Janitorial Service
  • Posted Date : 11/03/2021
  • Phone Number : 0111263307
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 12/16/2021

Description

 “የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ”

የህንፃ የውጭ ግድግዳ እና መስታወት የፅዳት አገልግሎት

ኩባንያችን ግሎባል ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መሥሪያ ቤቱ የሚገኘበትን ህንፃ አጠቃላይ የውጭ ግድግዳ እና መስታወት ለማፀዳት አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶችን በማወዳደር ለማሠራት ይፈልጋል። የሥራዎቹ ዝርዝር የሚከተለው ሰንጠረዥ ውስጥ ተገልፆ ቀርቧል፡፡

ተ/ቁ የአገልግሎት ዝርዝር መለኪያ ብዛት መግለጫ
 

1.

የኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት የሚገኘበትን ህንፃ አጠቃላይ የውጭ ግድግዳ እና መስታወት የፅዳት አገልግሎት  

በካሬ

የህንፃው አጠቃላይ የውጭ ግድግዳ እና መስታወት የካሬ ልኬት ተጫራቾች ህንፃውን በአካል ቀርበው በባለሞያችሁ ሰርቨይ እና ልኬት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 

በዚህ መሠረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም አገልግሎቱን የሚሰጡ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የታክስ ክሊራንስ ሰርትፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ሱማሌ ተራ በሚገኘው ግሎባል ኢንሹራንስ ህንፃ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ከፍል 3 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 3-58 የማይመለስ ብር 50.00 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከሰአት በኋላ እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በሰም የታሸገ የመጫረቻ ሰነዶቻችሁን በዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በ10ኛው ቀን ከሰአት በኋላ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡30 (ስምንት ተኩል) ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በሥራ ቀን ካልዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 ብር (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ፣ በባንክ ጋራንቲ ወይም በካሽ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. ድርጅታችን ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111-263-307 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ፡፡

አድራሻ: ሱማሌ ተራ ተክለሃይማኖት ሆስፒታል ፊት ለፊት ግሎባል ኢንሹራንስ ህንፃ

ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

Send me an email when this category has been updated