ለንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) የባለአክስዮኖች 19ኛ መደበኛ እና 14ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ

Announcement
Nib-Insurance-logo

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/03/2021
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/27/2021

Description

የስብሰባ ጥሪ

ለንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) ባለአክስዮኖች በሙሉ

በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 እና አንቀጽ 366 (1)፣367 (1)፣370 እና 393 እንዲሁም በኩባንያው መመስረቻ   ፅሁፍ አንቀጽ 8.2 (ለ)  መሠረት፣ የባለአክስዮኖች 19ኛ መደበኛ እና 14ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ህዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በሸራተን ሆቴል ላሊበላ አዳራሽ ስለሚደረግ በስብሰባው ላይ በሰዓቱ እንድትገኙ በአክብሮ እንጠይቃለን፡፡

19ኛ  ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፡-

 1. የጉባዔውን አጀንዳዎች ማፅደቅ፣
 2. የጉባዔውን ድምፅ ቆጣሪዎች መሰየም፣
 3. ምልዓተ ጉባዔ መሟላቱን ማረጋገጥ፣
 4. የጉባዔውን ጸሀፊ መምረጥ፣
 5. እ.ኤ.አ. የ2020/21 በጀት ዓመት የተደረጉ የኩባንያውን የአክሲዮን ዝውውሮችን ማፅደቅና አክስዮን የገዙ  አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፣
 6. እ.ኤ.አ የ2020/21 ዓመታዊ የዳይሬክተሮች ቦርድ  ሪፖርትን ማዳመጥ፣
 7. እ.ኤ.አ. የ2020/21 የውጭ ኦዲተሮችን ዓመታዊ ረፖርት ማዳመጥ፣
 8. በተራ ቁጥር 6 እና 7 በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ ሪፖርቶቹን ማፅደቅ፣
 9. እ.ኤ.አ የ2020/21 የኩባንያው የትርፍ ድልድል ላይ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ መወሰን፣
 10. እ.ኤ.አ የ2020/21 የውጭ ኦዲተሮችን የአገልግሎት ክፍያ መወሰን
 11. እ.ኤ.አ. የ2021/22 የዲሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ የሥራ ዋጋና የ2021/22 የዲሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበል ክፍያን መወሰን፣
 12. የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ ሪፖርት ማድመጥ እና የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ማከናወን
 13. የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ

የ14ኛው ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳ

 1. የጉባኤውን አጀንዳ ማፅደቅ፣
 2. የጉባኤውን ድምፅ ቆጣሪዎችን መሰየም፣
 3. የጉባኤውን ጸሀፊ መምረጥ
 4. ምልዓተ ጉባኤ መሟላቱን ማረጋገጥ፣
 5. የኩባንያውን ካፒታል ማሳደግ ላይ የተደረገ ማሻሻያን ተወያይቶ ማጽደቅ
 6. የጉባኤውን ቃለጉባኤ ማጽደቅ

ማሳሰቢያ፡-

 • ባለአክስዮኖች ለስብሰባ በሚመጡበት ጊዜ ማንነትን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ዋናውንና ቅጂውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • በጉባዔው ላይ በግንባር የማይገኙ ባለአክስዮኖች፣ በንግድ ሕግ አንቀጽ 373 መሠረት፣ በወኪሎቻቸው አማካይነት መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን፣ ጉባዔው ከመካሄዱ ከሦስት የሥራ ቀናት በፊት ደምበል ሲቲ ሴንተር 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት የፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 207 ቀርበው ለዚሁ ጉዳይ የተዘጋጀውን የውክልና መስጫ ቅፅ በመፈረም ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ በያዘ ተወካይ አማካይነት በጉባዔው ላይ መገኘት ይችላሉ፤
 • የባለአክስዮኖች ህጋዊ ወኪሎች ፡-
  • ማንነትን የሚያሳይ የራሳችሁን የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ዋናውንና ቅጂውን፣
  • የወካያችሁን የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም መንጃ ፈቃድ ወይም የፓስፖርት ቅጂ፣እንዲሁም በጉባዔው ለመካፈልና ድምጽ ለመስጠት  የሚያስችል የውክልና ስልጣን ማስረጃ ዋናውን እና ቅጂውን ይዛችሁ በመቅረብ በጉባዔው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፤
 • የስብሰባው ተሳታፊዎች የጤና ሚኒስቴር ያወጣውን የኮቪድ 19 መከላከያ መንገዶች በጥብቅ መተግበር ይኖርባቸዋል፡፡

የንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.)የዳይሬክተሮች ቦርድ

Send me an email when this category has been updated