ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) የባለአክሲዮኖች 12ኛ መደበኛ እና 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ

Announcement
Oromia-Insurance-Company-logo

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/03/2021
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/11/2021

Description

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.

የባለአክሲዮኖች 12 መደበኛ እና 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔዎች

የስብሰባ ጥሪ

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) የባለአክሲዮኖች 12 መደበኛ እና 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ታህሳስ 02 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ሸራተን አዲስ ሆቴል ላሊበላ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የኩባንያው ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በጉባዔዎቹ ላይ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ሀ. የባለአክሲዮኖች 12 መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፡-

 1. ረቂቅ አጀንዳዎችን ማጽደቅ፤
 2. የአዲስ አክሲዮን ሽያጭና የነባር አክሲዮን ዝውውርን መመልከት፤
 3. እ.አ.አ የ2020/21 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርትን ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
 4. እ.አ.አ የ2020/21 በጀት ዓመት የኩባንያውን የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
 5. የኩባንያውን እ.አ.አ በ2020/2021 በጀት ዓመት የተጣራ ትርፍ ክፍፍልን አስመልክቶ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
 6. የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበል እና ዓመታዊ ክፍያን መወሰን፤
 7. የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማጽደቅ፤

ለ. የባለአክሲዮኖች 8 አሰቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፡-

 1. ረቂቅ አጀንዳዎችን ማጽደቅ፤
 2. የኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. የመመስረቻ ፅሑፍን ስለማሻሻል፤
 3. የኩባንያውን ካፒታል ለማሳደግ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
 4. የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማጽደቅ፤

ማሳሰቢያ፡-

 • በጉባዔው ላይ በአካል መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ጉባዔው ከመካሄዱ ከሦስት ቀናት በፊት አፍሪካ ጎዳና፣ ሸዋ ዳቦ ፊት ለፊት፣ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ሕንፃ፣ 6ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው በኩባንያው ዋና መ/ቤት በመገኘት የእንደራሴ (Proxy) ቅጽ በመሙላት በምትወክሉት ወኪል አማካይነት በጉባዔው ላይ መሳተፍና ድምጽ መስጠት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
 • እንዲሁም፣ በጉባዔው ላይ ለመሳተፍና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል ሕጋዊ የውክልና ሥልጣን ዋናውንና አንድ ኮፒ ይዞ በሚቀርብ ወኪል በኩል በጉባዔው መካፈል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
 • በጉባዔው ላይ በአካል የምትገኙም ሆነ በኩባንያው ዋና መ/ቤት ቀርባችሁ ውክልና የምትሰጡ ባለአክሲዮኖች ማንነታችሁን የሚያሳይ ሕጋዊ ሰነድ (የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ) ዋናውንና አንድ ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ፣ እንዲሁም ሕጋዊ ውክልና ይዛችሁ የምትቀርቡ ተወካዮች የወካያችሁን ማንነት የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡

የኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.)

የዳይሬክተሮች ቦርድ

Send me an email when this category has been updated