ለብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) የባለአክስዮኖች 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ

Announcement
NICE-–-National-Insurance-Company-of-Ethiopia-s.c-logo-reportertenders

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/03/2021
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/27/2021

Description

የስብሰባ ጥሪ

ለብሔራዊኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (..)

ባለአክስዮኖች  በሙሉ

National Insurance Company of Ethiopia (NICE) S.C.

በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ ክፍል 2፤አንቀጽ 393፤ ቁጥር 1 መሠረት እንዲሁም በብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 2.2 እና 2.3 መሠረት የባለአክስዮኖች 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ቅዳሜ ሕዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል (Elilly International Hotel) ስለሚደረግ በስብሰባው ላይ እንድትገኙ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

የ28ኛ መደበኛ ጉባዔው አጀንዳ

 1. የጉባዔውን ጽ/ቤት አባላት መሰየም፤
 2. የጉባዔውን ፀሐፊ መሰየም፤
 3. የጉባዔውን ድምጽ ቆጣሪዎች መሰየም፤
 4. ምልዓተ ጉባዔ መማDላቱን ማረጋገጥ፤
 5. የጉባኤውን አጀንዳ ማጽደቅ፤
 6. የተደረጉ የአክስዮን ዝውውሮችን ማጽደቅና መቀበል፤
 7. እ.ኤ.አ. የ2020/2021 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ መወሰን፤
 8. እ.ኤ.አ. የ2020/2021 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት እና የሂሣብ መግለጫዎችን ማዳመጥ እና ተወያይቶ መወሰን፤
 9. ከ27ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በኃላ የተተኩ የቦርድ አባላትን ተቀብሎ ማጽደቅ፤
 10. እ.ኤ.አ. የ2020/2021 በጀት ዓመት የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈልን አስመልክቶ የዳይሬክተሮች ቦርድ ባቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
 11. እ.ኤ.አ. የ2020/2021 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
 12. እ.ኤ.አ. የ2021/2022 የውጭ ኦዲተሮችን ምርጫ ማካሄድ፤
 13. የዳይሬክተሮች ቦርድ እ.ኤ.አ. የ2020/2021 በጀት ዓመት ዓመታዊ ክፍያና የ2021/22 በጀት ዓመት ወርሃዊ አበል ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
 14. የስብሰባውን ቃለ-ጉባዔ ማጽደቅ፤

ማሳሰቢያ

 1. በጉባዔው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክስዮኖች ተወካይ በመሰየም መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ጉባዔው ከሚካሄድበት ቀን ቢያንስ ከ3 የሥራ ቀን በፊት በኩባንያው ዋና መ/ቤት 5ኛ ፎቅ የሕግ መምሪያ ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የውክልና መስጫ ቅጽ በመፈረም፤ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን ማስረጃ ዋናውን ከአንድ ኮፒ ጋር በስብሰባው ዕለት ይዞ በመቅረብ መሳተፍ ይቻላል፡፡
 2. ባለአከስዮኖቹም ሆኑ ተወካዮቹ ወደ ስብሰባው ቦታ ሲመጡ የራሳቸውን መታወቂያ ካርድ፤ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውንና ኮፒ ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው እናሳስባለን፡፡
 3. ተወካዮቹ የውጭ ዜጋ ከሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ እንዲያቀርቡ እንጠይቃለን፡፡
 4. በጤና ጥበቃ ኮቮድ ፕሮቶኮል መሰረት ማንኛውንም የስብሰባ ተሳታፊ ወደ ስብሰባው ቦታ ሲመጣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ) ማድረግ ይኖርበታል፡፡