የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ለዳቦ፣ ለፓስታ እና ማካሮኒ ማምረቻ በግብዓትነት የሚውል የስንዴ ዱቄት፤ የፎም ፍራሽ እና ትራስ፤ የገላ፣ የልብስ፣ ፈሳሽ እና የዱቄት ሳሙና እንዲሁም የመፀዳጃ ቤት ወረቀት በሀገር ውስጥ ከሚገኙ አምራቾች በማዕቀፍ የግዥ ስልት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Industrial-Inputs-Development-Enterprise-Logo

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 11/07/2021
 • Phone Number : 0113692647
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/26/2021

Description

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

የሸቀጥ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 011/14

ድርጅታችን በተለያዩ ቅርንጫፍ ማዕከላቱ በኩል ለተጠቃሚው ማህበረሰብ የሚያሰራጨውና በኢትዮጵያ የወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟላ፤

 • ለዳቦ፣ ለፓስታ እና ማካሮኒ ማምረቻ በግብዓትነት የሚውል የስንዴ ዱቄት፤ የፎም ፍራሽ እና ትራስ፤ የገላ፣ የልብስ፣ ፈሳሽ እና የዱቄት ሳሙና እንዲሁም የመፀዳጃ ቤት ወረቀት በሀገር ውስጥ ከሚገኙ አምራቾች በማዕቀፍ የግዥ ስልት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት  በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች

 1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የብቃት ማረጋገጫ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ያላቸው መሆን ይገባቸዋል፡፡
 2. በጨረታ መመሪያው ላይ የተቀመጡትን ግዴታዎች በሙሉ መወጣት የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
 3. ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ፒያሳ በተለምዶ አትክልት ተራ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስርያ ቤት የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በሚወዳደሩበት የምርት ዓይነት ልክ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ህዳር 17 ቀን 2014 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
 6. ጨረታው በተመሳሳይ ህዳር 17 ቀን 2014 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡10 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113-69-26-47/69-24-39