አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 11/07/2021
- Phone Number : 0115150711
- Source : Reporter
- Closing Date : 12/07/2021
Description
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ፣ ግብር ፣ በተጠቀሱት ንብረቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችንም ገዢ ይከፍላል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪውን የወደፊት የሊዝ ክፍያ ገዢ ይከፍላል፡፡
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል፡፡
- በባንኩ ብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
- የጨረታው ቦታ በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ላንቻ አካባቢ ህብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ከነበረው ህንጻ ጎን ካለው አልፓውሎ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በባንኩ ህግ መምሪያ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-150711 እና 0115 54 67 37 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
t.q$ |
ytbĶW SM |
ከተበዳሪው የሚፈለግበት
ቀሪ ዕዳ |
የመያዣ ስጪው ስም |
የንብረቶቹ ዓይነትና አገልግሎት | የቦታው ስፋት በካ.ሜ | የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የጨረታ
መነሻ ዋጋ በብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ
ሰዓት |
1 |
ወይ. መሰረት ዳኛቸው | እስከ ሀምሌ 05 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ብር 37,136,824.65 | ተበዳሪው | ለመኖሪያ ቤት | 299 | AA000090407934 | አ/አ ኮልፌ ቀራንዮ አንፎ | 12,140,261.00 | ህዳር 28 ቀን 2014 | 4፡30-5፡30 | 5፡30-6፡00 |
እስከ ሀምሌ 05 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ብር 37,136,824.65 | አቶ ነብየልሁል ደበበ | ለመኖሪያ ቤት | 200 | Sul/1047/2003 | ሱሉልታ | 2,014,421.92 | ህዳር 29 ቀን 2014 | 4፡30-5፡30 | 5፡30-6፡00 | ||
እስከ ሀምሌ 05 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ብር 37,136,824.65 | አቶ ጓዴ ምናየ | ለመኖሪያ ቤት | 200 | Wmmlmsu/974/07 | ሱሉልታ | 2,037,661.42 | ህዳር 30 ቀን 2014 | 4፡30-5፡30 | 5፡30-6:00 | ||
2 |
አቶ ሞላ ተመስገን |
እስከ ሚያዝያ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ብር15,400,000.00 | ተበዳሪው | G+2
መኖሪያ ቤት |
127.3 | AA0000907013827 | አዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ
ወረዳ 7 |
6,410,193.40 | ታህሳስ 1 ቀን 2014 ዓ.ም | 4፡30-5፡30 |
5፡30-6፡00 |